በ14 ክለቦች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2ኛ ዲቪዝዮን የሁለት ሳምንታት መርሐ ግብር እየቀረው ቻምፒዮኑን አሳውቋል።
ዛሬ ባህርዳር ላይ አዲስ አበባ ከተማን ያስተናገደው ጥረት ኮርፖሬት 2-0 ማሸነፍ ችሏል። በዚህም ነጥቡን 60 በማድረስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ከሚቀረው አርባምንጭ ከተማ በ13 ነጥቦች በመራቅ የውድድሩ አሸናፊ መሆኑን ከወዲሁ አረጋግጧል።
ባለፈው የውድድር ዓመት ቡድኑን ካፈረሰው ዳሽን ቢራ ላይ ሴቶች ቡድኑን ሙሉ ለሙሉ በመረከብ በውድድር ላይ መሳተፉን የቀጠለው ጥረት ኮርፖሬት በአመቱ ጠንካራ አቋሙን ያሳየ ሲሆን አመዛኙን ጊዜም በመሪነት መዝለቅ ችሏል።
በዛሬው እለት አአ ከተማ በጥረት ቢሸነፍም ወደ በጥሩነሽ ዲባባ አቻ መውጣት ምክንያት ጥረት እና አርባምንጭን ተከትሎ በቀጣዩ ዓመት ወደ አንደኛ ዲቪዝዮን ማደጉን ለማረጋገጥ ከሁለት ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ማግኘት በቂው ነው። በቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ወደ አንደኛ ዲቪዝዮን የሚያልፈው አራተኛ ቡድን የሚለይ ይሆናል። ኢትዮጵያ ቡና በ41 ፣ አካዳሚ በ40 ነጥቦች የተሻለ እድልን ሲይዙ ጥሩነሽ ዲባባ እና ልደታ ክ/ከተማ ሌሎች የማደግ እድል ያላቸው ቡድኖች ናቸው።
የዛሬ ውጤቶች
ጥረት ኮርፖሬት 2-0 አዲስ አበባ ከተማ
ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ 0-0 ኢትዮጵያ ቡና
ቂርቆስ ክ/ከተማ 0-2 ቦሌ ክ/ከተማ
ሻሸመኔ ከተማ 1-2 አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
ፋሲል ከተማ 1-1 አርባምንጭ ከተማ
ልደታ ክ/ከተማ 1-0 ቅድስት ማርያም ዩ.
ኢ/ወ/ስ አካዳሚ 1-0 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ
የደረጃ ሰንጠረዥ