የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎችን ቀን ለዋውጧል።
በ26ኛው ሳምንት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ሰኞ ዕለት በአዲስ አበባ ስታድየም በ09:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዲያ እና በ11፡30 መከላከያ ከ ጅማ አባጅፋር እንዲሁም ማክሰኞ እለት ደግሞ በ09:00 ኤሌክትሪክ ከ ሀዋሳ እና በ11:30 ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ እንዲጫወቱ አስቀድሞ መርሐ ግብር ቢወጣም በሁለት ጨዋታዎች ላይ ቀን የማቀያየር ስራ ተሰርቷል።
በዚህም መሠሰት ሰኞ የነበረው የመከላከያ እና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ሲሸጋገር ማክሰኞ የነበረው የኤሌክትሪክ እና ሀዋሳ ጨዋታ ወደ ሰኞ ተሸጋሽጓል። ፌዴሬሽኑ እነዚህን ጨዋታዎች ለማቀያየር እንደምክንያት ያስቀመጠው በ25ኛው ሳምንት ጅማ ስታድየም ላይ በጅማ እና ጊዮርጊስ ጨዋታ ላይ ከተከሰተው ስርዓት አልበኝነት ጋር በተያያዘ ሁለቱ ቡድኖች በተመሳሳይ ቀን በአንድ ሜዳ ላይ ጨዋታ ማድረጋቸው ሊያስከትለው የሚችለው ተጨማሪ ችግርን ለመከላከል በማሰብ እንደሆነ ታውቋል።
የተሻሻለው የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይህንን ይመስላል:-
ሰኞ ሰኔ 4 ቀን 2010
04:00 መቐለ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ (አአ)
09:00 ኤሌክትሪክ ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ)
09:00 ወልዋሎ ከ ደደቢት (ዓዲግራት)
09:00 አርባምንጭ ከ ወላይታ ድቻ (አርባምንጭ)
09:00 ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ይርጋለም)
11:30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዲያ (አአ)
ማክሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2010
09:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ (አአ)
12:00 መከላከያ ከ ጅማ አባ ጅፋር (አአ)