ሳላዲን ከመጀመርያ ልምምዱ በኋላ….

ሳላዲን ሰዒድ በትላንትናው እለት የመጀመርያ የአል አህሊ ልምምዱን ከሰራ በኋላ የተሰማውን ደስታ ገልጧል፡፡ የአፍሪካውን ትልቅ ቡድን አካል በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማውና በአጀማመሩም ደስተኛ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

ሳላዲን ከመጀመርያው ልምምድ በኋላ የቀዮቹ አሰልጣኝ ሁዋን ካርሎስ ጋሪዶ እንዳበረታቱት ለአህሊ ድረ-ገፅ ተናግሯል፡፡ ‹‹ ጋሪዶ ከልምምዱ በኋላ ያበረታቱኝ ሲሆን ከዚህ የተሸለ መሻሻል እንደሚገባኝም ነግረውኛል፡፡ ለአንድ ወር ያህል ከልምምድ እንደራቅክ አውቃለሁ፡፡ ወደ ቀድሞው የአካል ብቃትህ እና አቋምህ እንድትመለስ በጋራ እንሰራለን ብለውኛል ›› ብሏል፡፡

ሳላ ከቡድኑ ጋር በቶሎ ለመዋሃድ እና ቦታውን ለማስከበር የቻለውን እንደሚሰራ ጨምሮ ተናግሯል፡፡

ሳላዲን ከ3 ወራት በፊት ከሌላው የግብፅ ልከብ ዋዲ ዴግላ ወደ አል አህሊ በነፃ ዝውውር መዘዋወሩ የሚታወስ ሲሆን በአፍሪካ ውድድሮች ላይ ለዋዲ ዴግላ በመጨመወቱ ለአል አህሊ በሃገር ውስጥ ውድድሮች በመጫወት የ2014 የውድድር ዘመንን ይጨርሳል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ