አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በይፋ የዋሂዳ ሰንአ አሰልጣኝ ሆነዋል

ባለፈው ሳምንት የየመኑን ዋሂዳ ሰንአን ለማሰልጠን ከስምምነት ደርሰው የኮንትራት ስምምነት ለመፈራረም ወደ ሰንአ ያቀኑት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከክለቡ ጋር በይፋ ኮንትራት ተፈራርመዋል፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የኢትዮጵያ ፣ ከአል-ሳቅር ጋር ደግሞ የየመን ሊግ ዋንጫን ያሸነፉት አሰልጣኝ ስዩም በአዲሱ ክለባቸውም የተሸለ ውጤት ለማምጣት ተስፋ አድርገዋል፡፡

‹‹ በየመን ቆይታዬ በአል-ሳቅር ክለብ ታሪክ የመጀመርያ የሆነውን የሊጉን ዋንጫ አሸንፌያለው፡፡ አሁን ከ7 አመታት በኋላ ደግሞ ከዋሂዳ ሰንአ ክለብ እና ከፕሬዝዳንት አሚን ጋር በመሆን ትልቁን ስኬት ለማስመዝገብ መጥቻለሁ ›› ብለዋል፡፡

ለ2 አመት ከ8 ወራት በኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድንረዳት አሰልጣኝነት እና ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት የሰሩት ስዩም በየመን እግርኳስ ከሚከበሩ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ናቸው፡፡

ያጋሩ