ባሬቶ በመጀመርያ ጨዋታቸው ሽንፈት አስመዘገቡ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2015 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ከአንጎላ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ 1-0 ተሸንፏል፡፡ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነትን የተረከቡት አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶም በመጀመርያ ጨዋታቸው ሽንፈትን አስተናግደዋል፡፡

ኢትዮጵያ በጨዋታው በውጪ ሃገር የሚጫወቱት ጌታነህ ከበደ ፣ አዲስ ህንፃ እና ሳላዲን ሰኢድን ሳትይዝ ወደ ሜዳ የገባች ሲሆን ጨዋታው ተመጣጣኝ እና በጎል ሙከራዎች የታጀበ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአንጎላ የድል ግብ የተገኘችው ገና በ16ኛው ደቂቃ ሲሆን ግቧን ያስቆጠረው ፍሬድሪኮ ካስትሮ ዶሳንቶስ (ፍሬድ ) ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአንጎላ መልስ ወደ ብራዚል በማቅናት ከተለያዩ የብራዚል ክለቦች ጋር በሚያደርጋቸው የዝግጅት ጨዋታዎች በነሃሴ መጨረሻ ከአልጄርያ ጋር ለሚካሄደው ጨዋታ ዝግጅቷን ትቀጥላለች፡፡

ያጋሩ