ዋሊያዎቹ በሩዋንዳ ተሸንፈዋል

ለ2017 የጋቦን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በዝግጅት ላይ ያለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በወዳጅነት ጨዋታ በሩዋንዳ አቻው 3ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ብዙም ማራኪ ባልነበረው ጨዋታ ዋሊያዎቹ በሁለተኛው አጋማሽ በተከታታይ በተቆጠሩባቸው ግቦች ተሸንፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያ አሰላለፍ ይህንን ይመስል ነበር

አቤል ማሞ

ተካልኝ ደጀኔ ፣ ሙጂብ ቃሲም ፣ አስቻለው ታመነ ፣ ስዩም ተስፋዬ

አስቻለው ግርማ ፣ ብሩክ ቃልቦሬ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ ኤፍሬም አሻሞ

ባዬ ገዛኸኝ ፣ ኡመድ ኡኩሪ

11949537_708974639233707_1724654965_n

በኪጋሊ አማሆሮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ሩዋንዳዎች ናቸው፡፡ በ18ኛው ደቂቃ እርነስታ ሱጊራ ለሩዋንዳ ቀዳሚዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ዋሊያዎቹ የመጀመሪያው ግማሽ ሊጠናቀቅ 4 ደቂቃ ሲቀር በባዬ ገዛኸኝ የአቻነት ግብ አስቆጥረው የመጀመሪያው ግማሽ 1ለ1 ማጠናቀቅ ችለው ነበር፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ በ65ኛው ደቂቃ ጃን ባፕቲስት ሙዚንግራ እና በ73ኛው ደቂቃ ጃኪዊስ ቱዩሴንጌ ግብ ታግዘው ጨዋታውን 3ለ1 ማሸነፍ ችለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2ኛ የምድብ ማጣርያውን በያዝነው አመት መጨረሻ ከሲሸልስ ብሄራዊ ቡድ ጋር ያደርጋል፡፡

ያጋሩ