መከላከያ ማራኪ ወርቁን አስፈረመ

የክለቡ ቁልፍ አጥቂዎች የለቀቁበት መከላከያ በብሄራዊ ሊጉ ድንቅ አቋም ያሳየው ማራኪ ወርቁን ከሱሉልታ ከነማ አስፈርሟል፡፡

ፈጣኑ አጥቂ በባህርዳር በተከናወነው የብሄራወ ሊግ ጥሎ ማለፍ ውድድር ላይ የጨዋታው ኮከብ ተብለው ከተመረጡ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን ከሱሉልታ ጋርም እስከ ግማሽ ፍፃሜው ድረስ ዘልቋል፡፡

ጦሩ በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ሶስት አጥቂዎችን የለቀቀ ሲሆን መዳህኔ ታደሰ ወደ ዳሽን ፣ በዳሶ ሆራ ወደ አዳማ ከነማ እንዲሁም ማናዬ ፋንቱ ወደ መብራት ኃይል አምርተውበታል፡፡ የማራኪ መፈረም ወደ ቀድሞ ክለቡ ከተመለሰው መሃመድ ናስር ጋር ተደምሮ የአጥቂ ክፍሉን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መከላከያ ለማራኪ ዝውውር የ2 አመት 2 መቶ ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡

ያጋሩ