ደደቢት ራሱን ከኢትዮዽያ ዋንጫ አገለለ

ደደቢት በኢትዮጵያ ዋንጫ ሐሙስ ሰኔ 14 ጅማ ላይ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ሊያደርገው የታሰበውን ጨዋታ መሰረዙን ክለኩ በላከልን ደብዳቤ አሳውቋል።

የሁለት ጊዜ የውድድሩ ቻምፒዮን ደደቢት ራሱን ከውድድሩ ውጭ ለማድረጉ በምክንያትነት ያስቀመጠው በተደጋጋሚ ፌዴሬሽኑ የሚያወጣው የጨዋታ መርሀ ግብር የተዘበራረቀ እና ክለቡን ለአላስፈላጊ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ እንደሆነ በደብዳቤው የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ቀደምም እንደነዚህ ያሉ መሰል ስህተቶች እንዲታረሙ ጠይቆ ምላሽ ያላገኘ መሆኑን ገልፀዋል።

ደደቢት ከኢትዮጵያ ዋንጫው ጨዋታ 3 ቀናት በኋላ አዲስ አበባ ላይ በተስተካካይ ጨዋታ ከአርባምንጭ ጋር እንዲጫወት መርሐ ግርብ መውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመርያ ዙር እና ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ የሚካሄዱ ይሆናል፡፡


ረቡዕ ሰኔ 13 ቀን 2010

09፡00 መከላከያ ከ ድሬዳዋ ከተማ (አአ)

11፡30 ኤሌክትሪክ ከ መቐለ ከተማ (አአ)


ሀሙስ ሰኔ 14 ቀን 2010

09፡00 ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና (ሀዋሳ)

11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወላይታ ድቻ (አአ)


ሩብ ፍፃሜ

ሀሙስ ሰኔ 14 ቀን 2010

09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ)