በታንዛንያ አስተናጋጅነት ከ9 ቀናት በኋላ እንደሚምር የተነገረው የሴካፋ ካጋሜ ካፕ የክለቦች ውድድር ምድብ ድልድል ላይ ተካተው የነበሩት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ያንግ አፍሪካንስ ከውድድሩ ራሳቸውን አግልለው በሌሎች ክለቦች ተተክተዋል፡፡
እንደ ሶካ ኬንያ ዘገባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከውድድሩ ራሱን ያገለለበትን ምክንያት በይፋ ያላሳወቀ ቢሆንም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑና ውድድሩ በሚከናወንበት ወቅትም የለጉ ጨዋታዎች የማይጠናቀቁ በመሆኑ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ያንግ አፍሪካንስ በበኩሉ በካፍ ኮንፌሬሽንስ ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ በመሆኑ ከውድድሩ ራሱን ለማግለል መወሰኑ ተገልፃዋል፡፡
ሁለቱ ክለቦች ከውድድሩ ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ የታንዛንያው ሲንጊዳ እና የሩዋንዳው ኤፒአር ወደ ምድብ ድልድሉ ተካተዋል፡፡
ሙሉ ድልድል
ምድበ 1
አዛም (ታንዛኒያ)
ዩጋንዳ ክለብ
ጄኬዩ (ዛንዚባር)
ካቶር (ደቡብ ሱዳን
ምድብ 2
ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ)
ጎር ማሂያ (ኬንያ)
ሊዲያ ሉዲች (ቡሩንዲ)
ፖርትስ (ጅቡቲ)
ምድብ 3
ኤፒአር (ሩዋንዳ)
ሲምባ (ታንዛንያ)
ሲንጊዳ (ታንዛንያ)
ዳካዳህ (ሶማልያ)