የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዝዮን ተጠናቋል

የ2010 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ – ሁለተኛ ዲቪዝዮን ዛሬ ረፋድ ከተደረገ ጨዋታ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል።

በትላንትናው እለት ሊካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት የነበረው የፋሲል ከተማ እና የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ በዝናብ ምክንያት ወደ ዛሬ ረፋድ ተሸጋግሮ ፋሲል 2-1 ማሸነፍ ችሏል።

በትላንትናው እለት አስቀድሞ ቻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው ጥረት ኮርፖሬት ባህርዳር ላይ አቃቂ ቃሊቲን አስተናግዶ 2-0 በማሸነፍ የውድድር ዘመኑን በድል ሲያገባድድ የውድድሩን ዋንጫም ተረክቧል።

ትላንት ተስተካካይ ጨዋታውን ያደረገው አርባምንጭ ከተማ በሜዳው ቂርቆስን 3-0 በማሸነፍ ሁለተኛ ደረጃን በማግኘት የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሲሆን ወደ አሰላ ተጉዞ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን የገጠመው አዲስ አበባ ከተማ 2-1 በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል። ጥሩነሽ ዲባባ ደግሞ ወደ አንደኛ ዲቪዝዮኑ ያደገ አራተኛው ቡድን ሆኗል።

የ26ኛ ሳምንት ውጤቶች 


የ2010 ሙሉ ሰንጠረዥ