06:05 ጋዜጣዊ መግለጫው ተጠናቋል።
ለጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች
የቴክኒክ ጉዳዮች
አቶ ሰውነት ቢሻው – ከቀጣዩ አሰልጣኝ የምንጠብቀው ዝርዝር እቅድ የሚያቀርብ፣ እቅዱን የሚያስረዳ፣ እቅዱን ወደ ተግባር መለወጥ የሚችል ነው።
– የተሰራ፣ ተዘጋጅቶ የተቀመጠ አሰልጣኝ ካለ ጠቁሙኝ..
አቶ ሰውነት ቢሻው – ሁሉም ሰው ብሔራዊ ቡድኑ አሸናፊ እንዲሆን ይፈልጋል። እዚህ የተገኘሁት መስፈርቱ ላይ ክርክር ላደርግ ሳይሆን አንድ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ምን አይነት መሆን አለበት የሚለው ነው። ሀገራዊ ስሜቱ፣ ከተጫዋቾች ጋር ያለው ግንኙነት፣ ቀን ከሌት የመስራት አቅሙ፣ ፕሮፌሽናል አስተሳሰቡ፣ ብሔራዊ ቡድኑን የሚያደራጅበት መንገድ ሊታይ ይገባል። እውነት የዚህን አይነት ሰው አለን ወይ? እንዲህ አይነት ሰው ቢኖረን ከስራ ቅጥር ይልቅ ወደ ሹመት እናመራ ነበር።
አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ – የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት መስፈርቱነረ ያወጣነው ከኛ የተሻሉ ሀገራትን አሰራር በመመልከት ነው። ከነዚህ መካከል ትልቁ መስፈርት በማሰልጠን ያሳለፈው ጊዜ እና ልምድ ነው። ለዛ ነው 10 ዓመት ልምድ የሆነበት ምክንያት። መስፈርቱ ትክክለኛ ነው ብለን እናምናለን።
*ስለ ክለብ አደረጃጀት
– ውድድሮች እንደተጠናቀቁ በክለብ አደረጃጀት ዙርያ ከክለቦች ጋር ውይይት እናደርጋለን።
*የገንዘብ እጥረት
– የገንዘብ እጥረትን ለመፍታት የገቢ አማራጮች ላይ ስራ እንሰራለን። ከነዚህ በላይ ግን ከፍተኛ ገቢ የሚገኘው ከስፖንሰር ስለሆነ ገፅታችንን ማሻሻል ላይ እናተኩራለን።
*ብሔር እና እግርኳስ
– ይህን ችግር ለመፍታት ከመንግስት የተለያዩ አካላት ጋር ውይይት እያደረግን እንገኛለን።
*ብሔራዊ ቡድን
-የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝን በቅጥር ማስታወቂ ለማውጣት የወሰንነው ስራ አስፈፃሚው በተስማማበት አካሄድ ነው።
– ከካፍ እና ፊፋ አመራሮች ጋር በተገናኘንባቸው አጋጣሚዎች የቴክኒክ ዲፓርትመንት ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል። በአንድ ጊዜ አንድ ግለሰብ ከመሾም ይልቅ የለውጡ አካል አድርገን የተደራጀ ቴክኒክ ዲፓርትመንት እንዲኖረን ነው ያሰብነው።
* እቅድ ስለመተግበር
ስጋታችሁ ይገባኛል። የሪፎርም እቅዶችን በአግባቡ ወደ ተግባር ማዋል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። እያንዳንዳንዱ ኃላፊነት የሚሰጠው አካል የተሰጠነን የስራ ድርሻ በአግባቡ መወጣት አለበት።
ጥናት ተጠንቶ የሚቀርበው ዶክመንትን ለሚመለከተው አካል ሁሉ ለገፃ እንዲደረግ እና ሂስ እንዲሰጥበት እናደርጋለን።
የጥናት ቡድኑ አባላት ቁጥር እንዲያንስ የተደረገው በቶሎ ወደ ስራ ለመግባት ከማሰብ አንፃር ነው።
*ውድድር – ፌዴሬሽኑን በተረከብን ማግስት ስብሰባ አድርገን ውድድሮች በሰላም እንዲጠናቀቁ ተነጋግረናል። ዳኞችን አወያይተን አቅጣጫ አስቀምጠናል።
* ስፖርታዊ ጨዋነት – በጊዜያዊነት ፈጣን እርምጃ የሚሹ ስራዎችን ከመስራት በተጨማሪ ይህን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት እንቅስቃሴ እያደረግን ነው። ውድድሮች እንዳለቁ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቶች እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ድረስ በመሄድ ችግሩን ለመፍታት አስበናል።
– እኛ ፌዴሬሽኑን በተረከብን ማግስት በጅማ አባጅፋር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላይ ከፍተኛ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ተከተስቶ ነበር። እንዲህ አይነት ክስተቶች ላይ የፍትህ አካላት ውሳኔ የመጨረሻው ሊሆን አይገባም። ዘላቂ እርቅ መፈጠር አለበት በሚል የሁለቱን ክለቦች አመራሮች ለማናገር ሰኔ 25 ቀጠሮ ይዘናል። ይህ በጣም ትልቅ ምሳሌ መሆን የሚችል ነው።
– የትግራይ እና አማራ ክልል ቡድኖች እርስ በእርስ የሚያደርጉትን ጨዋታ በየሜዳቸው እንዲያደርጉ ከክልል አመራሮች ጋር ተነጋግረን መፍትሄ ለማስቀመጥ እንቅስቃሴ ጀምረናል።
* ብሔራዊ ቡድን – ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው አቶ ሰውነትን ኃላፊነት በመስጠት የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቅጥር ለመፈፀም እየተንቀሳቀስን ነው።
– ስራ አስፈፃሚዎች የብሔራዊ ቡድን የቡድን መሪ የመሆን አሰራር መቀረት ይኖርበታል።
* አደረጃጀት – የስራ አስፈፃሚ እና የማኔጅመንት የእለት ተእለት ስራ ተቀላቅሏል። ፌዴሬሽን በተለያዩ ሙያዎች ስብጥር የሚዋቀር ስለሆነ ለእያንዳንዱ ስራ ባለሙያ የመመደብ ስራ ይሰራል። በአንድ ጀንበር ለውጥ ባይመጣ እንኳን አንድ እርሾ አስቀምጠን ማለፍ እንችላለን።
* ሪፎርም – ይህ ተቋም ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። በሶስት መሰረታዊ የሪፎርም ስራዎች ላይ ማለትም የአመራር፣ የአሰራር እና የባለድርሻ አካላት ያልተገደበ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ እቅድ ይቀርባል። የሊግ አደረጃጀት፣ የመተዳደርያ ድንብ፣ የክለብ አደረጃጀት፣ ማኔጅመንት እና እያንዳንዱን ችግር በጥልቀት የሚያጠና ቡድንን አቋቁመን በአንድ ወር ውስጥ “Mother Document” እንዲዘጋጅ አቅጣጫ አስቀምጠናል።
* አቶ ኢሳይያስ ጂራ – ” ፌዴሬሽኑን ከተረከብን ጊዜ አንስቶ ባለፈው አንድ ወር በ5 ዋና ዋና ጉዳየች ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን እንኛለን።”
1 የተጀመሩ ውድድሮች በሚጠናቀቁበት አካሄድ
2 የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር በመሰረታዊነት የመፍታት
3 ብሔራዊ ቡድን
4 የጽህፈት ቤት ግዢ
5 አጠቃላይ መዋቅራዊ ማሻሻያ (Reform) ናቸው።
*አቶ ኢሳይያስ – ገፅታ ግንባታ ላይ ስራ መስራት ይኖርብናል። በፌዴሬሽኑ የተሰሩ ስራ ስራዎች እንዳሉ ሆነው ያልተሰሩ ስራዎች ገፅታውን አበላሽቶታል። የገፅታው መበላሸት ደግሞ የገበያ ዋጋውን አውርዶታል። ገፅታ እኔ ስለፈለግኩ ብቻ የሚስተካከል ሳይሆን በጠንካራ ስራ የሚገኝ ነው።
04:20 መግለጫው በአቶ ኢሳይያስ ጂራ ማበረራርያ ተጀምሯል። ፕሬዝዳንቱ የመጀመርያው ጋዘዜጣዊ መግለጫ እንደመጠራ ያስፈለገው “ፌዴሬሽኑን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ስለተሰሩ ስራዎች ለሚድያ ይፋ ለማድረግ ነው።” ብለዋል።
በመግለጫው ላይ ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳይያስ ጂራ፣:ስራ አስፈፃሚዎቹ አቶ ሠውነት ቢሻው፣ አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ፣:አቶ አበበ ገላጋይ እና የፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ ተገኝተዋል።