‹‹ በእግርኳስ እንደዚህ አይነት ውጤቶች ይከሰታሉ ›› ዮሃንስ ሳህሌ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምድብ 10 ሁለተኛ ጨዋታውን ከሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን ጋር አድርጎ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን ፈፅሟል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ከሲሸልስ የእግርኳስ ደረጃ ዝቅተኝነት እና በርካታ ደጋፊዎችን ይዞ ወደ ቪክቶርያ በማቅናቱ ምክንያት በብዙዎች ዘንድ የአሸናፊነት ግምት ቢሰጠውም ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ተገዷል፡፡ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም ያገኙትን አጋጣሚ ባለመጠቀማቸው ነጥብ ተጋርተው እንደወጡ ተናግረዋል፡፡

‹‹ በሁለቱም የጨዋታ ክፍለ ጊዜዎች ያገኘናቸውን የግብ ማግባት አጋጣሚዎች አለመጠቀማችን ዋጋ አስከፍሎናል፡፡ ያም ሆኖ አቻ ውጤቱ ብዙም የሚስከፋ አይደለም፡፡ በዚህ ውጤት ማንንም ተጠያቂ ማድረግ አልፈልግም፡፡ በቀጣይ ስህተቶቻችንን አርመን ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን›› ብለዋል፡፡

ዮሃንስ ሳህሌ ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየት ሲሰጡ - ፎቶ በ ድሬ ቲዩብ
ዮሃንስ ሳህሌ ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየት ሲሰጡ – ፎቶ በ ድሬ ቲዩብ

ከትንሷ ሲሸልስ ጋር ነጥብ መጋራታቸው በእግርኳስ የሚጋጥም ክስተት እንደሆነም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ጠቁመዋል፡፡

‹‹ ምክንያት መደርደር አያስፈልግም፡፡ ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች ወደ ግብ ብንቀይር ኖሮ ጨዋታውን አሸንፈን መውጣት እችል ነበር፡፡ እንደዚህ አይነት ውጤቶች ደግሞ በእግርኳስ ያጋጥማሉ፡፡ በጨዋታው ልንሸነፍባቸው የምንችልባቸው አጋጣሚዎችም ተፈጥረው ነበር፡፡ ›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ያጋሩ