በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን 14ኛው ሳምንት ያልተከናወኑት የመከላካያ እና ደደቢት እንዲሁም የሀዋሳ እና ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፎርፌ ውሳኔ አስተላልፏል።
የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ስፍራው ድረስ በመጓዝ ለውድድሩ ዝግጁ ቢሆንም የሀዋሳ ቡድን በቦታው ሳይገኙ የቀሩ ሲሆን ንግድ ባንክም በሁኔታው ቅሬታውን መግለፁ የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ መከላከያ ከደደቢት ጋር ሊደረግ በነበረው ጨዋታ በስፍራው ላይ ሳይገኝ መቅረቱም የሚታወስ ነው። ክስተቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለደደቢት እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፎርፌ አሸናፊነት ውሳኔ አስተላልፏል።
ውሳኔውን ተከትሎ አንድ ሳምንት በሚቀረው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ደደቢት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለውን የ3 ነጥብ እና 11 የጎል ልዩነት በማስጠበቅ ለ3ኛ ተከታታይ ዓመት ቻምፒዮን መሆኑን ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ አረጋግጧል። ንግድ ባንክ ቻምፒዮን ለመሆን በመጨረሻው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስን በሰፊ ጎል ልዩነት አሸንፎ ደደቢት በጌዴኦ ዲላ በሰፊ ልዩነት ተሸንፎ የ11 ጎል ልዩነቱ መቀየር ይኖርበታል።
ቅዳሜ በሚደረገው የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ ለሶስተኛ ደረጃ የሚደረገው ፉክክር ይጠበቃል። መከላካያ እና ሀዋሳ ተመሳሳይ ነጥቦችን ይዘው በአንድ የግብ ልዩነት መከላከያ በልጦ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቅዳሜ በሚደረገው ጨዋታ የ3ኛ ደረጃ ባለቤቱ የሚለይ ይሆናል።
የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር
ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን 2010
08:00 ደደቢት ከ ጌዴኦ ዲላ (አአ ስታድየም)
08:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢት. ንግድ ባንክ (ባንክ ሜዳ)
09:00 ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ (ይርጋለም)
09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ኤሌክትሪክ (ድሬዳዋ)
10:00 መከላካያ ከ አዳማ ከተማ (ባንክ ሜዳ)
የደረጃ ሰንጠረዥ