በ2011 ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚያድጉ 6 ቡድኖችን የሚለየው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ከሐምሌ 16 – ነሀሴ 2 በአዳማ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አታውቋል።
የኢትዮዽያ አንደኛ ሊግ የ2010 የውድድር ዓመት መደበኛው የዙር ውድድር 57 ቡድኖች መካከል በአምስት ምድብ ተከፍሎ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ረፋድ በተደረጉ የምድብ ሠ ጨዋታዎች ፍፃሜውን አግኝቷል። ወደ ማጠቃለያው ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡት 16 ቡድኖችም ሙሉ ለሙሉ ታውቀዋል።
ወደ ማጠቃለያ ውድድሩ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች የሚከተሉት ናቸው፡-
ቱሉ ቦሎ ከተማ፣ አራዳ ክ/ከተማ፣ አሶሳ ከተማ፣ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ፣ ሞጆ ከተማ፣ ገላን ከተማ፣ ራያ አዘቦ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ዳሞት ከተማ፣ ጎጃም ደብረማርቆስ፣ ናኖ ሁርቡ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርሲ ነገሌ፣ ሺንሺቾ ከተማ እና ትግራይ ውሀ ስራ (በአማካይ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበ ጥሩ 4ኛ)
ከውድድሩ መክፈቻ ቀን አስቀድሞ ሐምሌ 15 በ09:00 ላይ በአዳማ የምድብ ድልድሉ የሚወጣ ሲሆን ውድድሩ በአዳማ አበበ ቢቃላ ስታድየም የሚካሄድ ይሆናል።.