2007 ተገባዶ 2008ን ልንቀበል የቀሩን 5 ቀናት ብቻ ናቸው፡፡ እየተገባደደ ባለው 2007 በእግርኳሳችን ውስጥ በርካታ ክንውኖች ተከናውነዋል ፣ አነጋጋሪ ክስተቶች ተከስተዋል ፣ አስደሳች እና አሳዛኝ አጋጣሚዎች ተከስተዋል ፣ በርካታ ግለሰቦች እና ተቋማትም በ2007 በእግርኳሳችን መነጋገርያ ሆነዋል፡፡

በሃገር ውስጥ የእግርኳስ ጉዳዮች ላይ የምትሰራው ሶከር ኢትዮጵያም የ2007 አመት መገባደድን አስመልክቶ የአመቱ ሰው ወይም ተቋምን ለመምረጥ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡ በምርጫው አንደኛ የሚወጣው ግለሰብ ወይም ተቋም የሶከር ኢትዮጵያ የአመቱ ሰው / ተቋም በሚል ማስታወሻ የሚበረከትለት ሲሆን በምርጫው ውስጥ የተካተቱ ሰዎች እና ተቋማትን ያካተተ ሰፊ ፅሁፍ ይቀርባል፡፡

በዚህ ምርጫ ላይ አንባቢዎቻችን እንዲሳተፉ እየጋበዝን በሃሳብ መስጫው ላይ በአመቱ ተጽእኖ ፈጥረዋል ብለው ያመኑባቸውን ሰዎች እና ተቋማት ማስፈር ይችላሉ፡፡

በ2007 በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በበጎም ይሁን በአሉታዊ መልኩ ተፅዕኖ አሳርፈዋል ተብለው በሶከር ኢትዮጵያ ኤዲተሮች ከተመረጡ ግለሰቦች እና ተቋማት መካከል መሰረት ማኒ ፣ ዋልያ ቢራ ፣ የሴቶች ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ባህርዳር ስታዲየም እና የከተማው ህዝብ ፣ ሎዛ አበራ ፣ ዮሃንስ ሳህሌ ፣ ሳሚ ሳኑሚ ፣ አዳማ ከነማ ፣ በኃይሉ አሰፋ ፣ ጋቶች ፓኖም እና ዘሪሁን ሸንገታ/ፋሲል ተካልኝ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ለእርስዎ በ2007 በእግርኳሳችን ላይ በበጎም ይሁን በአሉተታዊ መልኩ በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ የራሱን ተፅዕኖ አሳርፏል የሚሉት ማንን ነው?

በሃሳብ መስጫው ላይ ያስፍሩልን፡-

 

ያጋሩ