የ2010 የኢትዮጵያ ዋንጫ አንድ የሩብ ፍፃሜ፣ የግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ ጨዋታዎች በመጪው ዓመት መጀመርያ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።
በአንደኛ ዙር ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና እና በሩብ ፍፃሜው ጅማ አባጅፋር ከ ኤሌክትሪክ የሚያደርጉት ጨዋታ በፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች መሸጋሸግ ምክንያት ወደ ሐምሌ 12 ሲሸጋገሩ መከላከያ ከፋሲል ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ በተያዘለት እለት ሐምሌ 10 አዳማ ላይ ይከናወናል።
ፌዴሬሽኑ እንደገለጸው ከላይ ከተጠቀሱት ጨዋታዎቸ ውጪ የሚደረጉት ማለትም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ እና ሲዳማ አሸናፊ የሚያደርገው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ፣ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች እና የፍፃሜው ጨዋታዎች በ2011 የሚካሄዱ ይሆናል።
ለዘመናት የተዘነጋ ውድድር የሆነው የኢትዮጵያ ዋንጫ ወደ ቀጣይ የውድድር ዓመት ሲራዘም የአሁኑ የመጀመርያ አይደለም። በ2007 መጠናቀቅ ያልቻለው ውድድር በ2008 መጀመርያ መጠናቀቁም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።