ከነሐሴ 4 – 20 በታንዛንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣርያ ከቀናት በኋላ ዝግጅቱን የሚጀምረው ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ለ25 ተጨዋቾች የመጀመርያ ጥሪ አድርገዋል።
ጥሪ ከተደረገላቸው 25 ተጫዋቾች መካከል በባቱ በተካሄደው የ17 ዓመት በታች የማጠቃለያ ውድድር ላይ ጥሩ አቋማቸውን ያሳዩ 15 ተጫዋቾች የመጀመርያ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው ሲሆን የቀሩት አስሩ ተጨዋቾች በሚያዚያ ወር በቡሩንዲ አስተናጋጅነት በተካሄደው የሴካፋ ዋንጫ የተካፈሉ ተጨዋቾች ናቸው። እስከ ፊታችን ሐሙስ ድረስ በአአ ብሉ ስካይ ሆቴል ማረፊያቸውን በማድረግ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ልምምድ ሲያደርጉ ይቆዩና አርብ የሙሉ ጊዜ ዝግጅታቸውን ለማድረግ ወደ ሀዋሳ ከተማ የሚያቀኑ ይሆናል። ከቀናት በኋላም አምስት ተጫዋቾችን በመቀነስ ወደ ታዛንያ የሚያቀኑ የመጨረሻዎቹ የ20 ተጨዋቾችን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ለታንዛኒያው ውድድር የተመረጡት 25 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው።
ግብ ጠባቂዎች ( 3)
ምንተስኖት ጊምቦ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ተስፋሁን አዲሴ (አዳማ ከተማ)፣ አብነት ይስሐቅ (ወላይታ ድቻ)
ተከላካዮች (6)
ዳግም ወንድሙ፣ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ጸጋአብ ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ረጃብ ሚፊታ (ማራቶን) አዛርያስ አቤል (ወላይታ ድቻ)፣ እንድርያስ ነገሰ ( አፍሮ ፅዮን)፣ ሔኖክ አወቀ (አፍሮ ፅዮን)
አማካዮች (11)
ሳሙኤል ጃጊሶ (ወላይታ ድቻ)፣ ሐጎስ ኃይሌ (መከላከያ)፣ ኦባንግ ኦፓንግ (አካዳሚ) ዮሐንስ ፋንታሁን ( አዳማ ከተማ)፣ ወንድማገኝ ኃይሌ (ሀዋሳ ከተማ)፣ አበባየሁ ሀጂሶ ( ወላይታ ዲቻ)፣ ምንተስኖት እንድርያስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሙሀባ አደም (ሲዳማ ቡና)፣ ተስፋሁን ሰቦቅሳ (መከላከያ)፣ ሙሉቀን ታደሰ ( ሀዋሳ ከተማ)፣ ናኦል ተስፋዬ (ስዊድን)
አጥቂዎች (5)
አላሚን ከድር (አዳማ ከተማ)፣ የዓብቃል ፈረጃ (አአ ከተማ)፣ አደም አባስ (አካዳሚ)፣ በየነ ባንጃው (አፍሮፅዮን)፣ አቤል ደንቡ ( አዳማ ከተማ)