የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰብያ ውድድር ሐምሌ 27 ይጀምራል

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አዘጋጅነት ለክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያነት የሚካሄደው ውድድር ሐምሌ 27 ይጀመራል።

ለ13ኛ ተከታታይ ዓመት ክቡር ይድነቃቸው ተሰማን ለመዘከር በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበት አዘጋጅነት የሚዘጋጀው የታዳጊዎች ውድድር ከሐምሌ 27 ጀምሮ ምንም አይነት የውድድር ዕድል ያላገኙ ዕድሜያቸው ከ14 – 15 ዓመት በሆኑ ታዳጊዎች የሚካሄድ ሲሆን እስከ ሐምሌ 24 ቀን የእድሜ ተገቢነትን የማጣራት ስራ ተከናውኖ ሐምሌ 25 ቀን በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የምድብ ድልድል የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት የሚካሄድ ይሆናል ።

የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ ውድድር ላለፉት 12 ዓመታት ሲዘጋጅ በርካታ ለክለብ እና ለብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻሉ ተጫዋቾች እንደወጡበት ይታወቃል። ለዚህም ማሳያ ምንተስኖት አዳነ፣ ናትናኤል ዘለቀ፣ ሳምሶን ጥላሁን፣ ኤልያስ ማሞ፣ ሳላዲን በርጌቾ፣ አህመድ ረሺድ፣ አቡበከር ሳኒ፣ ዮሴፍ ዳሙዬ እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።