የሴካፋ ዋንጫ አራተኛ ቀን ጨዋታዎች በዛሬው እለት ሲከናወኑ ኢትዮጵያ ተከታታይ ሁለተኛ ድሏን በማስመዝገብ ለዋንጫው የተሻለ እድልን ጨብጣለች።
09:00 ላይ ኬንያን የገጠመችው ኢትዮጵያ በመሠሉ አበራ ብቸኛ ጎል 1-0 አሸንፋለች። የቅዱስ ጊዮርጊሷ ተከላካይ ሰኞ እለት ኢትዮጵያ ሩዋንዳን ስታሸንፍ ጎል አስቆጥራ የነበረ ሲሆን ዛሬም የማሸነፍያውን ጎል አስቆጥራለች። ድሉን ተከትሎ ሉሲዎቹ ቀጣዩ ጨዋታ እስኪደረግ ድረስ በ6 ነጥቦች የደረጃ ሰንጠረዡን ቢመሩም ዩጋንዳ ከሩዋንዳ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይታ መሪነቱን በድጋሚ ተረክባለች።
ውድድሩ አርብ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ታንዛንያን ማሸነፍ በቀጥታ የዋንጫ ባለቤት ሲያደርጋት አቻ ከተለያየች ሩዋንዳ ከኬንያ ነጥብ መጣል ወይም ከ5 የጎል ልዩነት በታች ማሸነፍ ኢትዮጵያን ለመጀመርያ ጊዜ ቻምፒዮን ያደርጋታል።
የመጨረሻ እለት መርሐ ግብር
አርብ ሐምሌ 20 ቀን 2010
09:00 ኢትዮጵያ ከ ታንዛንያ
11:15 ሩዋንዳ ከ ኬንያ
የደረጃ ሰንጠረዥ