አርባምንጭ ከተማ መሳይ ተፈሪን አሰልጣኝ አድርጎ ቀጠረ

ከ7 የውድድር ዓመታት በኋላ ከሊጉ የወረደው አርባምንጭ ከተማ መሳይ ተፈሪን ቀጣዩ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ወላይታ ድቻን ለ9 ዓመታት ከብሔራዊ ሊግ ጀምሮ እስከ ፕሪምየር ሊጉ አብረው ከቆዩ በኋላ በዘንድሮው የውድድር ዓመት አጋማሽ ክለቡን ለቀው በፋሲል ከተማ ያለፉትን አራት ወራት ቆይታ አድርገዋል። አሁን ደግሞ በተጫዋቾችነት ወዳሳለፉበት ከተማ በመመለስ አርባምንጭ ከተማን በአንድ ዓመት ውል ለማሰልጠን ተስማምተዋል።

የአዞዎቹ ስራ አስኪያጅ አቶ ታዲዮስ ጨመሳ ለሶከር ኢትዮጵያ “አሰልጣኙን ስንሾም በቶሎ ለመመለስ በማሰብ ነው። ይህን ደግሞ ለማድረግ የአካባቢው ባህል እና የአጨዋወት መንገድ በመረዳት እንዲሁም ካለው ልምድ አንፃር ተነስተን ይህን ክለብ ያለጥርጥር እንደሚመለስ እምነት ስላለን ነው።” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አሰልጣኙም ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመመለስ አላማ ይዘው እንደተቀላቀሉ ገልፀዋል።

ያጋሩ