ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል

ሊጉን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሁለት ተጫዋቾችን ፊርማ ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል። 

ኄኖክ አዱኛ ከአንድ ዓመት የጅማ አባ ጅፋር የተሳካ ቆይታ በኋላ ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል። የቀኝ መስመር ተከላካዩ በክረምተለ ድሬዳዋ ከተማን ለቆ ወደ ጅማ ካመራ በኋላ ወጥ አቋም በማሳየት ከክበሉ ጋር የፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን መሆን ችሏል። የሁለት ዓመት ኮንትራት በፈረመበት ቅዱስ ጊዮርጊስም ከሌላው ጥሩ የውድድር ዓመት ካሳለፈው አብደለልከሪም መሐመድ ጋር የሚፎካከር ይሆናል።

ሌላው ለክለቡ የፈረመው ተጫዋች አቤል ያለው ነው። ወጣቱ አጥቂ በደደቢት ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ የግማሽ ዓመት በፋሲል ከተማ የውሰት ቆይታን ጨምሮ እድገት ሲያሳይ የነበረ ሲሆን በተለይ በመጀመርያው የውድድር ዓመት አጋማሽ አስደናቂ ጊዜ ማሳለፍ ችሎ ነበር። እንደ ኄኖክ ሁሉ አቤልም የሁለት ዓመት ኮንትራት ፈርሟል።