ፊሊፕ ኦቮኖ በመቐለ ከተማ ውሉን አድሷል

የንባብ ቆይታ:27 ሰከንድ

ኤኳቶሪያል ጊኒያዊው ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ኦቮኖ በመቐለ ከተማ ለተጨማሪ 1 ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል፡፡ ኦቮኖ በመጀመሪያ ዓመት የኢትዮጵያ ቆይታው ስኬታማ ጊዜያትን ከመቐለ ከተማ ጋር አሳልፏል፡፡

ኦቮኖ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይመለሳል የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም ባልተጠቀሰ ከፍተኛ ደሞዝ በመቐለ ከተማ የነበረውን ውል አድሷል፡፡ ኦቮኖ በቋሚነት በክለቡ አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን አነስተኛ መጠን ግብ ካስተናገዱ ክለቦች መካከል አንዱ ለሆነው የመቐለ ከተማ ጠንካራ የመከላከል አደረጃጀት ተጨማሪ ጥንካሬን ፈጥሯል፡፡

በኦርላንዶ ፓይሬትስ ተጠባባቂ የነበረው ኦቮኖ በመቐለ ከተማ ያሳየውን ጥሩ እንቅስቃሴ ተከትሎ በግንቦት ወር ሃገሩ ማቻኮስ ላይ ከኬንያ ጋር ባደረገችው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ለብሄራዊ ቡድን መጠራቱ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ