በግንቦት ወር ወደ ኃላፊነት የመጣው አዲሱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ሰይሟል።
7 ቋሚ ኮሚቴዎች ያሉት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት የሚከተሉት ናቸው:-
የቴክኒክ እና ልማት ኮሚቴ – ኢ/ር ሰውነት ቢሻው
የብሔራዊ ውድድሮች አዘጋጅ ኮሚቴ
የፕሪምየር ሊግ – ኮ/ል አወል አብዱራሂም
የከፍተኛ ሊግ – አቶ ኢብራሂም መሐመድ
የአንደኛ ሊግ – አብዱራዛቅ ሐሰን
የሴቶች እግርኳስ ልማት ኮሚቴ – ወ/ሮ ሶፊያ አልማሙን
የዳኞች እና ታዛቢዎች ኮሚቴ – አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ
የማርኬቲንግ ኮሚቴ – አቶ አበበ ገላጋይ
የፀጥታ ኮሚቴ – አቶ አሊሚራህ መሐመድ
የህክምና ኮሚቴ – አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ
በሹመቱ መሰረት ባለፈው የፌዴሬሽን ስልጣን ዘመን ሰብሳቢ የነበሩ 5 ግለሰቦች አሁንም በሌላ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ሲሰየሙ 4 ግለሰቦች ደግሞ ለሹመቱ አዲስ ናቸው።
ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም በሰጠው መግለጫ ስራዎች በባለሙያዎች እንደሚሰሩ መገለፁ የሚታወስ ሲሆች በተሰየሙት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ስር በምክትል ሰብሳቢነት ባለሙያዎች እንደሚካተቱ ታውቋል።
በፌዴሬሽኑ መተዳደርያ ደንብ መሰረት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ከስራ አስፈፃሚ አባላት ሲመረጡ የፍትህ አካላት (የዲሲፕሊን ኮሚቴ እና የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ) እንዲሁም የኦዲት የቁጥጥር ኮሚቴ ከፌዴሬሽኑ ውጪ የሆኑ ገለልተኛ ግለሰቦች ይሰየማሉ።