ወልዋሎ አራተኛ ተጫዋች አስፈርሟል

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አማኑኤል ጎበናን የክለቡ 4ኛ ፈራሚ አድርጎ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። 

አማኑኤል አርባምንጭ ከተማን በአምበልነት ሲመራ የቆየ ሲሆን የውል ዘመኑ መጠነመቀቁን ተከትሎ ለጥቂት ወራት አብሯቸው የሰራው አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን በወልዋሎ ተቀላቅሏቸዋል። የመሀል አማካዩ ቢጫ ለባሾቹን የተቀላቀለው በአንድ ዓመት ውል ነው።

ወልዋሎ በዝውውር መስኮቱ ከአማኑኤል በፊት ቢንያም ሲራጅ፣ ብርሀኑ ቦጋለ እና ዳንኤል አድሃኖምን አስፈርሟል።