ባዬ ገዛኸኝ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል

ከቀናት በፊት ከሲዳማ ቡና ጋር የተለያየው ባዬ ገዛኸኝ ወደ ቀድሞ ክለቡ ወላይታ ድቻ የሚመልሰውን ዝውውር አድርጓል። 

የአጥቂ መስመር ተሰላፊው በዓመቱ መጀመርያ መከላከያን ለቆ ሲዳማ ቡናንገሁለት ዓመት ውል ቢቀላቀልም ከክለቡ ጋር በፈጠረው ያለመግባባት ውሉ ሳይጠናቀቅ መለያየቱ የሚታወስ ነው። ይህን ተከትሎም በብዙ የእግርኳስ ቤተሰብ ዓይን ውስጥ ወደገባበት ወላይታ ድቻ ከ3 ዓመት በኋላ ተመልሷል። በ2006 ወደ ሊጉ በመጣበት ዓመት ብዙዎችን ያስገረመው የወላይታ ድታ ስብስብ ውስጥ አባል የነበረው ባዬ በ2008 መከላከያን ተቀላቅሎ ለሁለት ዓመታት መቆየት ችሎ ነበር።

ባዬ በድቻ የሁለት ዓመት ኮንትራት የፈረመ ሲሆን ከኄኖክ ኢሳይያስ፣ አወል ዓብደላ፣ ታሪክ ጌትነት፣ ሳምሶን ቆልቻ እና ፀጋዬ አበራ በመቀጠል የክለቡ 6ኛ አዲስ ፈራሚ ሆኗል።