አሚን አስካር ከጉዳት ተመልሷል


ፈጣኑ የመስመር አማካይ አሚን አስካር ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ወደ ልምምድ ተመልሷል፡፡ ኦገስት 8 በቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉት ደርሶበት የነበረ ሲሆን ከ3 እስከ 6 ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገምቶ ነበር፡፡

የብራን ኤፍሲ አማካይ በፍጥነት ወደ ልምምድ በመመለሱ እንደተገረመ ለባ.ኖ ድረ-ገፅ ተናግሯል፡፡ ‹‹ እንዲህ በፍጥነት እመለሳለሁ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ እንቅስቃሴ መጀመሬ አስደስቶኛል፡፡ አሁን ምንም አይነት የህመም ስሜት አይሰማኝም ›› ብሏል፡፡

አሚን ወደ ልምምድ ቢመለስም ለጥቂት ቀናት እረፍት እንደሚያደርግ የክለቡ ዶክተር ካንት ፊልድስጋርድ ተናግረዋል፡፡ ብራን በቀጣዩ ቅዳሜ ከቫሌሬንጋ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ አሚን አይሰለፍም፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የ28 አመት ተጫዋች በአሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ጥሪ እንደተደረገለት ቢነገርም በተጫዋቹም ሆነ በፌዴሬሽኑ ማረጋገጫ አልተገኘም፡፡

በተያያዘ አሚን የአዘርባጃኑ ክለብ ካባላኒን አሚን አስካርን ለማዘዋወር ፍላጎት አሳይቷል፡፡

ያጋሩ