ወደ ፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን ለመጓዝ እንደተስማማ ባለፉት ቀናት ሲነገር የተቆየው ኤልያስ ማሞ በይፋ የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች ሆኗል።
በክረምቱ ወሳኝ ተጫዋቾችን የለቀቀው ጅማ አባ ጅፋር ልምድ ባላቸው ተጫዋቾች ክፍተቱን ለመሙላት የቆረጠ ይመስላል። በአማካይ ክፍሉ መስዑድ መሐመድ እና ኄኖክ ገምተሳን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ ሌላው ልመረድ ያለው አማካይ ኤልያስ ማሞ ጅማ ደርሷል። በ2000 በቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ኤልያስ በ2003 ወደ ንግድ ባንክ አምርቶ ለ4 ዓመታት ከቆየ በኋላ በ2007 ወደ ኢትዮጵያ ቡና ካመራ በኋላ ያለፉትን 4 የውድድር ዘመናት በቡና መቆየት ችሏል።
ጅማ አባጅፋር እስካሁን ኤልያስን ጨምሮ 8 ተጫዋቾችን አስፈርሟል።