ወደ አንደኛ ሊግ የሚያድጉ ክለቦችን ለመለየት የሚከናወነው የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና በሀዋሳ ከተማ ከነሀሴ 6 ጀምሮ ይካሄዳል።
ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባገኘነው መረጃ መሠረት 33 ክለቦች በውድድሩ የሚካፈሉ ሲሆን የሁለት ክለቦች (*) መካፈል እስካሁን አልተረጋገጠም። 6 ክልሎች እና ሁለት የከተማ አስተዳደር ክለቦችም ይሳተፋሉ።
ተሳታፊ ክለቦች የሚከተሉት ናቸው፡-
አዲስ አበባ (7) – ካልዲስ ኮፊ፣ ኮልፊ ቀራንዮ፣ የቄራ አንበሳ፣ ሲልቫ፣ አ.አ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት፣ ኢሰማ፣ ቴክኖ ሞባይል
ኦሮሚያ (5) – ዶዶላ ከተማ፣ አሰላ ከተማ፣ ገርበ ጉራቻ ከተማ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ፣ ኩርቻ ከተማ
አማራ (5) – ጎንደር ውሃ ስራ፣ ቡሬ ከተማ፣ ዳንግላ ከተማ፣ ገንደ ውሃ፣ ቆቦ ከተማ
ደቡብ (5) – ሾኔ ከተማ፣ ሀዳሮ ከተማ፣ አንጋች ከተማ፣ አንሌሞ ወረዳ፣ አረካ ከተማ
ትግራይ (3) – መቐለ ከተማ ቢ፣ ወልዋሎ ቢ፣ ገንፍል ውቅሮ ከተማ
ቤንሻንጉል (4) – መንጌ ቤንሻንጉል፣ ሶጌ ከተማ፣ ግልገል በለስ ከተማ፣ መተከል ፖሊስ
ድሬዳዋ (3) – ዋልያ፣ ድሬ ካባ፣ ገንደ ተስፋ
ጋምቤላ (3) – መኩዬ ከተማ፣ አልዋሮ ከተማ*፣ ናንልቾ*
የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ በነገው እለት 08:00 ላይ ሲካሄድ የመክፈቻ ጨዋታዎች ደግሞ እሁድ ይከናወናሉ።
ፎቶ – የአምና የውድድሩ አሸናፊ ጉለሌ ክፍለከተማ