የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ቅድመ ውድድር ዝግጅት መረጃዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2010 የውድድር ዘመን ከተጠናቀቀ አንድ ወር አስቆጥሯል። አመዛኞቹ ክለቦችም ከነሀሴ 13 ጀምሮ ለተጫዋቾቻው እረፍት የሰጡ ሲሆን በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ራሳቸውን እያዘጋጁ ይገኛሉ። ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቦቹ በሰበሰበቻቸው መረጃዎች አብዛኛዎቹ ክለቦች የዝግጅት ከተሞቻቸውን፣ የመሰብሰቢያ ቀናት እና የዝግጅት መጀመርያ ቀናትን የወሰኑ ሲሆን ቀሪዎቹ ክለቦች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ የሚወስኑ ይሆናል።

ክለቦቹ በቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው እስከ 6 ሳምንታት የሚዘልቅ ሲሆን የከፍተኛ ሊግ ውድድር አለመጠናቀቅን ተከትሎ በሶስቱ አዳዲስ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ምክንያት ከ6 ሳምንትም ሊረዝም ይችላል።


የቅድመ ውድድር ዝግጅት መረጃዎች