ወልዲያ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወረደውና በቀጣዩ የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊግ የሚሳተፈው ወልዲያ ስፖርት ክለብ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

2009 የውድድር ዓመትን በዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ጀምሮ በእገዳ ምክንያት በዘላለም ሽፈራው እየተመራ ያገባደደው ወልዲያ የቅጥር ማስታወቂያ በማውጣት አሰልጣኞችን አወዳድሮ በመጨረሻም አረጋዊ ወንድሙን መርጧል።

አሰልጣኝ አረጋዊ ወንድሙ ከዚህ ቀደም በእህል ንግድ፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና ጥቁር ዓባይ መስራታቸውን ክለቡ ጨምሮ ገልጿል።