ከነሀሴ 17 ጀምሮ በባቱ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የኮፓ ኮካ ኮላ ሀገር አቀፍ ከ15 ዓመት በታች ውድድር በዛሬው እለት ፍፃሜውን ሲያገኝ በሁለቱም ጾታ ኦሮሚያ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
ጠዋት 02:00 ባቱ ስታድየም ላይ በኦሮሚያ እና አዲስ አበባ መካከል በተደረገው የሴቶች የፍፃሜ ጨዋታ ኦሮሚያ 3-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። በተመሳሳይ ሰዓት ባቱ ት/ቤት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደቡብ አማራን 3-0 አሸንፎ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።
ቀጥሎ 04:00 ላይ በአማራ እና ኦሮሚያ መካከል የተከናወነው የፍፃሜ ጨዋታ በኦሮሚያ 6-1 የበላይነት ተጠናቋል። በተመሳሳይ ሰዓት በተከናወነው የደረጃ ጨዋታ ደግሞ ደቡብ ከጋምቤላ መደበኛውን ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በማጠናቀቃቸው በመለያ ምቶች ደቡብ አሸንፏል።
ከጨዋታዎቹ ፍፃሜ በኋላ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና የኮካ ኮላ የአፍሪካ ቀንድ ብራንድ ማኔጀር ወ/ት ትዕግስት ጌቱ ንግግር ካደረጉ በኋላ የሽልማት ስነስርዓት ተከናውኗል።
በወንዶች የተከናወኑ ሽልማቶች
ምርጥ ግብ ጠባቂ – ኛንግ አቤል (ጋምቤላ)
ከፍተኛ ገል አስቆጣሪ – አገኘሁ መስፍን (ኦሮሚያ – 4 ጎሎች)
ምርጥ ተጫዋች – ኤድመንድ ሞገስ (ኦሮሚያ)
ምርጥ አሰልጣኝ – አናንያ ዘለቀ (ኦሮሚያ)
የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ – ጋምቤላ
ተገቢ እድሜ በማቅረብ – ጋምቤላ
ልዩ የተገቢ እድሜ ተሸላሚ – ኦባንግ ማክ (ጋምቤላ)
3ኛ – ደቡብ (ዋንጫ፣ ነሀስ ሜዳልያ እና 20 ሺህ ብር)
2ኛ – አማራ (ዋንጫ፣ ብር ሜዳልያ እና 30 ሺህ ብር)
1ኛ – ኦሮሚያ (ዋንጫ፣ ወርቅ ሜዳልያ እና 50 ሺህ ብር)
በሴቶች የተከናወኑ ሽልማቶች
ምርጥ ግብ ጠባቂ – በረከት ዘመድኩን
ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ – ሔለን ዘብዲዮስ (ደቡብ – 6 ጎሎች)
ምርጥ ተጫዋች – ኢማን ሻፊ (አዲስ አበባ)
ምርጥ አሰልጣኝ – ታዬ መኮንን (ኦሮሚያ)
የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ – አማራ
ተገቢ እድሜ በማቅረብ – አዲስ አበባ
3ኛ – ደቡብ (ዋንጫ፣ ነሀስ ሜዳልያ እና 20 ሺህ ብር)
2ኛ – አዲስ አበባ (ዋንጫ፣ ብር ሜዳልያ እና 30 ሺህ ብር)
3ኛ – ኦሮሚያ (ዋንጫ፣ ወርቅ ሜዳልያ እና 50 ሺህ ብር)