ኢትዮጵያ ከ ሴራሊዮን – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

እሁድ ጳጉሜ 4 ቀን 2010


FT ኢትዮጵያ 1-0 ሴራሊዮን

35′ ጌታነህ ከበደ

ዋና ዋና ሁነቶች


ተጠናቀቀ!!!

* ኢትዮጵያ የመጀመርያ የምድብ ጨዋታ ድሏን በማሳካት በሶስት ነጥብ ከሌሎቹ የምድበ ሀገራት ጋር እኩል ነጥብ መያዝ ችላለች።

90′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

ጋቶች ፓኖም (ወጣ)
አማኑኤል ዮሀንስ (ገባ)


ተጨማሪ ደቂቃ – 4


86′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
ቢንያም በላይ (ወጣ)
ዳዋ ሆቴሳ (ገባ)


82′ ኢትዮጵያ የመጀመርያ ሶስት ነጠረቧን ለማግኘት 8 ደቂቃዎች ቀርተውታል። ጨዋታው በሴራሊዮን የሜዳ ክፍል አመዝኖ በመካሄድ ላይ ይገኛል።


78′ ጋቶች ከሴራሊዮን ተከላካዮች የነጠቀውን ኳስ ያገኘው ጌታነህ ከበደ ወደ ግብ በመጠጋት ከግብ ጠባቂው ቅርብ ርቀት በቀጥታ ቢመታውም የግቡ የግራ ቋሚን ለትማ ተመልሳለች። አስቆጪ ሙከራ!


72′ አቤል ያለው ከመስመር እየገፋ ገብቶ ወደ ውስጥ ያሻገረውን ኳስ ነፃ አቋቀም ላይ የነበረው ቢንያም ከማግኘቱ ቀድሞ የሴራሊዮን ተከላካይ ዴቪድ ሲምቦ ተንሸራቶ አውጥቶታል።


የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

70′ ዑመድ ኡኩሪ (ወጣ)
አቤል ያለው (ገባ)


የተጫዋች ለውጥ – ሴራሊዮን

68′ ሃሰን ሚላ ሲሴይ። (ወጣ)
ኦስማን ካካይ (ገባ)


67′ ሴራሊዮኖች ከማዕዘን በተሻማ ኳስ አስደንጋጭ የግብ እድል ቢፈጥሩም በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ በተፈጠረ ትርምስ ኳሱ ወደ ውጪ ወጥቷል።


65′ ጌታነህ፣ ሽመልስ እና ቢንያም በጥሩ አንድ ሁለት ቅብብል ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በጥቂት አጋጣሚዎች ቢጠጉም የመጨረሻ ኳሶች ስኬታማ ሲሆኑ አልታዩም።


60′ የተጫዋች ለውጥ – ሴራሊዮን
መሐመድ ቡያ ቱራይ (ወጣ)
ጆን ካማራ (ገባ)


57′ ጌታነህ ከበደ ጀርባውን ለተከላካዮች ሰጥቶ ኳሱን ከተቀበለ በኋላ በጥሩ ሁኔታ በመዞር ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል። ጥሩ ሙከራ!

ከአንድ ደቁቃ በኋላ ጌታነህ በድጋሚ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው መልሶበታል።


54′ የተጫዋች ለውጥ – ሴራሊዮን

ክዋሜ ክዌ (ወጣ)

ክርስቲያን ሞስስ (ገባ)


53′ በግራ ጎል ጀርባ የሚገኙትና የሲዳማ ቡና መለያ የለበሱ ደጋፊዎች በድንቅ አደጋገፍ ስታድየሙን እያደመቁት ይገኛሉ።


ተጀመረ!
11:17 ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል።


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በኢትዮጵያ መሪነት ተጠናቋል።



ተጨማሪ ደቂቃ – 1 ደቂቃ


ጎልልል!!!!
35′ ጌታነህ ከበደ የፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ለውጦታል። 1-0


ፍፁም ቅጣት ምት!
33′
በአህመድ ረሺድ ላይ በተሰራ ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት ለኢትዮጵያ ተሰጥቷል። ጌታነህ ሊመታ ነው።


30′ ጨዋታው የተቀዛቀዘ እና በተደጋጋሚ ፊሽካ የሚቆራረጥ ሆኗል።


24′ ኪይ ካማራ ከሳጥኑ ጠርዝ የመታውን ኳስ ሳምሶን በቀላሉ ተቆጣጥሮታል።


20′ የኢትዮጵያ ቅብብሎች የሴራሊዮን ሳጥን ሲደርሱ በተደጋጋሚ እየተቋረጡ ይገኛሉ።


13′ ዋልያዎቹ በሁለቱ የመስመር አጥቂዎች አማካኝነት የሚፈጠሩ እድሎች በቀላሉ እየባከኑ ይገኛሉ።


8′ ኢትዮጵያ በሴራሊዮን የሜዳ አጋማሽ ላይ አመዝና እየተጫወተች ትገኛለች።


6′ ዑመድ ኡኩሪ በሳጥኑ ቀኝ በኩል ወደ ግብ የመታው ኳስ የውጪኛውን መረብ ታኮ ወጥቷል። የመጀመርያ የግብ አጋጣሚ!


5′ ኢትዮጵያ በ4-2-3-1 አሰላለፍ ገብታለች። ከአራቱ ተከላካዮች ፊት ጋቶች እና ሙሉዓለም ሲጣመሩ ከሁለቱ የተከላካይ አማካዮች ፊት ሽመልስ በመሀል፣ ቢኒያም በግራ፣ ዑመድ በቀኝ መስመር ጌታነህ ደግሞ ከሶስቱ ፊት ተሰልፏል።


ተጀመረ!
10:12
ጨዋታው በጌታነህ ከበደ አማካኝነት ተጀምሯል።


* ኢትዮጵያ ከቀኝ ወደ ግራ ስታጠቃ ሴራሊዮን ከግራ ወደ ቀኝ ታጠቃለች።


* በስታድየሙ የፊት ለፊት እና በትሪቡን በኩል ያሉ የመቀመጫ ቦታዎች በተመልካች ሲሞሉ ከጎል ጀርባ የሚገኙት መቀመጫዎች በከፊል በተመልካች ተሞልቷል።


10:09 ተጫዋቾች ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ።


10:07 የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ላይ ይገኛል።


10:05 የሴራሊዮን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ላይ ይገኛል።


10:03 ሁለቱም ቡድኖች እና ጨዋታውን የሚመሩ ዳኞች በካፍ ኦፈለሴላዊ መዝሙር ታጅበውወደ ሜዳ ገብተዋል።


* የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት ኮ/ል አወል አብዱራሂም፣ ዘሪሁን ቀቀቦ እና ሰውነት ቢሻው እንዲሁም የደቡብ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ እማ ሌሎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።


09:50 የዋልያዎቹ ተጫዋቾች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ሲገቡ የሴራሊዮን ተጫዋቾች ዘግይተው ወደ ሜዳ ወጥተው ጥቂት እንዳሟሟቁ ተመልሰው ገብተዋል።


09:20 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሜዳ ገብቶ በማሟሟቅ ላይ ይገኛሉ።

አሰላለፍ

ኢትዮጵያ


1 ሳምሶን አሰፋ
2 አ/ከሪም መሐመድ
15 አስቻለው ታመነ
4 አንተነህ ተስፋዬ
3 አህመድ ረሺድ
6 ጋቶች ፓኖም
20 ሙሉዓለም መስ.
18 ሸመልስ በቀለ
10 ቢንያም በላይ
9 ጌታነህ ከበደ
11 ዑመድ ኡኩሪ


ተጠባባቂዎች


ተ/ማርያም ሻንቆ
ጽዮን መርዕድ
ሙጂብ ቃሲም
ኄኖክ አዱኛ
አምሳሉ ጥላሁን
ናትናኤል ዘለቀ
አማኑኤል ዮሀንስ
አዲስ ግደይ
አቤል ያለው
በኃይሉ አሰፋ
ዳዋ ሁቴሳ

ሴራሊዮን


1 ዞምቦ ሞሪስ
11 ሃሰን ሚላ ሲሴይ
18 ዴቪድ ሲምቦ
5 አሊ ሲሴይ
15 የዓሚ ዱኒያ
4 ሜዶ ካማራ
3 ቡያ ቱራይ
13 አልፍሬድ ሳንኮህ
7 ክዋሜ ክዌ
10 ኪይ ካማራ
9 አልሃሰን ካማራ


ተጠባባቂዎች


አልሃጂ ሲሴይ
መሐመድ ካማራ
ኡማሩ ባንጉራ
አቡ ሱማ
ኦስማን ካካይ
ማይክል ላሁውድ
ጆን ካማራ
ጁሊየስ ዎባይ
ኢብራሂም ኮንቴህ
ሼካ ፎፋና
አማዱ ባካዮኮ
ክርስቲያን ሞስስ


ዳኞች


ዋና ዳኛ | ሳዶክ ሴሌሚ (ቱኒዚያ)
1ኛ ረዳት | አቲያ አምሳድ (ሊቢያ)
2ኛ ረዳት | አይመን ኢስማይል (ቱኒዚያ)