አዳማ ከተማ አዲስ ምክትል አሰልጣኝ ቀጥሯል
አዳማ ከተማ ከአንድ ወር በፊት ሲሳይ አብርሀምን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በቀጠረበት ወቅት ዳዊት ታደሰን በምክትልነት መቅጠሩን ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ሆኖም አሰልጣኝ ዳዊት በውል ጉዳይ ላይ ከስምምነት ባለመድረሳቸው ክለቡ ሌላ ምክትል አሰልጣኝ ሲፈልግ ቆይቶ ደጉ ዱባለን መቅጠሩን አስታውቋል።
በመተሐራ ስኳር፣ ኢትኮ፣ ፐልፕ እና ወረቀት፣ ወንጂ ስኳር፣ አየር መንገድ፣ ጉና ንግድ፣ ሙገር ሲሚንቶ እና ሐረር ቢራ በተጫዋችነት ያሳለፉት አሰልጣኝ ደጉ ከ2001 ጀምሮ በወጣት ቡድን አሰልጣኝነት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በዋናው ቡድን አሰልጣኝነት ሲሰሩ ቆይተዋል። አሰልጣኙ በአዳማ ከተማ ለቀጣዮቹ ሁለት የውድድር ዓመታት የሲሳይ አብርሀም ረዳት ሆነው እንደሚሰሩ ለማወቅ ተችሏል።
በተያያዘ ዜና ዝግጅታቸውን ካልጀመሩ ክለቦች መካከል አንዱ የነበረው አዳማ ከተማ ነገ መስከረም 3 በባቱ (ዝዋይ) ከተማ የዝግጅት ጊዜውን የሚጀምር ሲሆን ከ25 እስከ 30 ቀናትን በከተማው ቆይታ ያደርጋሉ ተብሏል።
ተዛማጅ ፅሁፎች
የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ውሎ
የ2014 የአንደኛ ሊግ የማጠቃልያ ውድድር ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው አዲስ ከተማ፣ ሮቤ ፣ ዱራሜ እና ጂንካ ወደ ከፍተኛ ሊግ...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 0-0 ወላይታ ድቻ
ያለጎል ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኃላ አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ- አርባምንጭ ከተማ ስለጨዋታው “የመጀመርያው አጋማሽ በተቻለ መልኩ ለማጥቃት ጥረት...
ሪፖርት | ፉክክር አልባው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
የግብ ሙከራዎች ባልነበሩበት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። አርባምንጭ ከተማዎች ሀዋሳን ከረታው ስብስብ ባደረጓቸው ሁለት...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 3-0 ሰበታ ከተማ
ለሰባ አራት ደቂቃዎች በጎዶሎ ተጫዋቾች የተጫወተው አዳማ ከተማ ሶስት ነጥብ ካገኘበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ...
ሪፖርት | አዳማ ከ11 ጨዋታ በኋላ አሸንፏል
በረፋዱ ጨዋታ ለ73 ያክል ደቂቃዎች በጎዶሎ የተጫዋች ቁጥር ያሳለፉት አዳማ ከተማዎች በውድድር ዘመኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሦስት ግቦችን ባስቆጠሩበት ጨዋታ ከ11...
የ2014 የሴቶች ከፍተኛ ሊግ በንፋስ ስልክ ላፍቶ አሸናፊነት ተጠናቋል
በአስራ አራት ክለቦች መካከል ከታህሳስ 16 ጀምሮ ሲደረግ የነበረው የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ሁለት ክለቦችን ወደ ፕሪምየር ሊጉ በማሳደግ ተጠናቋል፡፡ በኢትዮጵያ...