የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ በፊት ከሚከናወኑ ውድድሮች አንዱ የሆነው የአማራ ዋንጫ ጥቅምት መጀመርያ ላይ ለማካሄድ እንደታቀደ ታውቋል።
በ2009 ከተደረገ በኋላ ባለፈው ዓመት ሳይከናወን የቀረው ውድድር ዘንድሮ በክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን፣ ኤቢ ማስታወቂያ እና ሳራ ትሬዲንግ ትብብር የሚከናወን ይሆናል። በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም የሚከናወነው ይህ ውድድር ከሌሎች መሰል ውድድሮች የተለየ አካሄድ በመከተል በዙር መልክ ተከናውኖ በነጥብ ከፍተኛ የሆነው ክለብ ቻምፒዮን ይሆናል።
ከጥቅምት 3-11 ለማከናወን የታሰበው ውድድር ላይ የሚካፈሉት ክለቦች እስካሁን እንዳልተለዩ ነገር ግን ባህር ዳር ከተማ፣ ፋሲል ከነማ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና የመሳሰሉ ክለቦችን ለማሳተፍ እንደታሰበ አዘጋጆቹ ገልፀዋል።