ደረጀ በላይን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመሾም ለቀጣይ የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ 14 ተጫዋቾን በአንድ ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታውቋል።
ክለቡ አሰልጣኝ ደረጀን የከፍተኛ ሊጉ መጠናቀቂያ ጨዋታዎች ላይ የቀጠረ እንደመሆኑ አሰልጣኙ በቡድኑ የሚቆዩትን አና የሚለቁትን ተጫዋቾች ቀደም ብለው እንዲለዩ አስተዋፅኦ አበርክቶላቸዋል።
ክለቡ ያስፈረማቸው 14 አዳዲስ ተጫዋቾች እና የነበሩበት ክለብ ይህን ይመስላል:-
ግብ ጠባቂዎች ፡ ደረጀ ዓለሙ (ወልዲያ)፣ ተሾመ ታደሰ (ሺንሺቾ)
ተከላካዮች ፡ ደጀኔ (ነቀምት ከተማ)፣ ሰለሞን ብሩ (ባህርዳር)፣ መሐመድ ሻፊ (ኢትዮጽያ መድን)፣ ተመስገን ደረሰ (ጅማ አባ ቡና)
አማካዮች ፡ ዳንኤል ገበየሁ (ኢትዮጽያ መድን)፣ ሙሴ እንዳለ (አዲስ አበባ ከተማ)፣ ዘላለም መላኩ (ቤንች ማጂ ቡና)፣ ወልዳይ ገብረእግዚአብሔር (ወሎ ኮምቦልቻ)፣ ታደለ አቡሌ (ሀምበሪቾ)
አጥቂዎች፡ ኤፍሬም ታምራት (ሺንሺቾ)፣ ኤሪክ ኮልማን (ወልዲያ/ቤንችማጂ)፣ አሳልፈው መኮንን (ወልዲያ)
ፎቶ ፡ (ከግራ ወደ ቀኝ) – ኤሪክ ኮልማን፣ አሳልፈው መኮንን እና ደረጄ ዓለሙ