ሽረ እንዳሥላሴ ኪዳኔ አሰፋን አስፈረመ

በመለያ ጨዋታ ጅማ አባ ቡናን አሸንፎ ወደ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ሽረ እንዳሥላሴ በዝውውር መስኮቱ ዘግይቶ በመቀላቀል በዚህ ሳምንት አራት ተጫዋቾች ማስፈረሙ ይታወሳል። ክለቡ አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረሙን በመቀጠል አንድ ተጫዋች የግሉ አድርጓል።

ኪዳኔ አሰፋ  ሽረን የተቀላቀለ አምስተኛ ተጫዋች ነው። ኪዳኔ በጅማ አባ ቡና ለዓመታት የነበረው ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ደደቢት ለማምራት በእጅጉ ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ማረፊያው ሽረ እንዳሥላሴ ሆኗል። የመስመር አጥቂው በአንድ ዓመት ውል ነው የሰሜን ኢትዮጵያውን ክለብ የተቀላቀለው።

ሽረ እንዳሥላሴ ከኪዳኔ በተጨማሪ ሰለሞን ገ/መድህን፣ ደሳለኝ ደበሽ፣ ኢብራሒማ ፎፋና እና ዲሜጥሮስ ወልደስላሴን ከዚህ ቀደም ማስፈረሙ የሚታወስ ነው።

በተያያዘ ዜና ሽረ እንዳሥላሴ የኤሌክትሪክ ተጫዋች የነበረው ኄኖክ ካሳሁንን ለማስፈም ከጫፍ ደርሷል።