የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ – ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2011


FT ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 መከላከያ

መለያ ምቶች : 2-3

-አስቻለው (አስቆጠረ)
-ጋዲሳ (አስቆጠረ)
-በኃይሉ (ሳተ)
-ናትናኤል (ተመለሰበት)
-ጌታነህ (ተመለሰበት)
-ምንይሉ (አስቆጠረ)
-ሽመልስ (አግዳሚ መለሰበት)
-ዳዊት እስ. (ተመለሰበት)
-ተመስገን (አስቆጠረ)
-አበበ (አስቆጠረ)

ተጠናቀቀ

– መከላከያ በመለያ ምቶች 3-2 አሸንፎ በታሪኩ ለ14ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ዋንጫ ቻምፒዮን ሆኗል።

ጨዋታው ያለግብ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምቶች ያመራሉ። ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በመለያ ምቶች ይለያል። 

ተጨማሪ ደቂቃ – 3

88′ ጋዲሳ መብራቴ በአቤል ያለው ተቀይሮ ገብቷል።

85′ ምንተስኖት አዳነ በምንይሉ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

80′ ምንይሉ በድጋሚ ግልፅ እድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

77′ ጌታነህ ከበደ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል።

70′ በእንቅስቃሴ ረገድ ከመጀመርያው አጋማሽ የተለየ ነገር ባይኖርም በርካታ የግብ አጋጣሚዎች በዚህ አጋማሽ እየተፈጠሩ ይገኛሉ።

68′ ምንይሉ ከግማሽ ጨረቃ ወደ ግብ የመታው ኳስ በአግዳሚው በኩል ለጥቂት ወጥቷል።

67′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

በአስር ቁጥር ቦታ ላይ የተሰለፈው አቡበከር ሳኒ ወጥቶ ታደለ መንገሻ ገብቷል።

66′ ጌታነህ ከበደ ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል።

63′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱሰ ጊዮርጊስ

ኄኖክ አዱኛ በመሐሪ መና ተቀይሮ ገብቷል። ኄኖክ በቀኑስ ጊዮርጊስ ማልያ የመጀመርያ ጨዋታው ነው።

62′ ሳሙኤል ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ምንይሉ በነፃ አቋቋም ላይ ሆኖ ቢያገኘውም በአግባቡ መቆጣጠር ሳይችል ለዓለም ይዞበታል።

59′ መሐሪ መና በጉዳት ከሜዳ ወጥቷል። ኄኖክ ተክቶ ለመግባት ልብስ በመቀየር ላይ ይገኛል።

53′ ተመስገን ጀርባውን ለተከላካይ ሰጥቶ በጥሩ ሁኔታ ያመቻቸለትን ኳስ ከግቡ ፊት ለፊት የነበረው ምንይሉ መትቶ ኢላማውን ስቷል። አስቆጪ እድል!

10:18 – ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ።



የመጀመርያው አጋማሸ ያለ ግብ ተጠናቀቀ።
ተጨማሪ ደቂቃ – 1

44′ መከላከያዎች ጥሩ የግብ አጋጣሚ መፍጠር ቢችሉም ምንይሉ የመታውን ኳስ በቀላሉ ለዓለም ተቆጣጥሮታል።

40′ ጌታነህ ከበደ የመታውን ኳስ ይድነቃቸው መልሶበታል። እስካሁን ከተደረጉት የተሻለ የጎል ሙከራ ነበር።

38′ ጨዋታው ደቂቃ እየገፋ በሔደ ቁጥር ይበልጥ እየተቀዛቀዘ ይገኛል።

36′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ፍሬው ሰለሞን ወጥቶ ዳዊት ማሞ ገብቷል።

22′ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ4-2-3-1፣ መከላከያ ደግሞ በ4-1-3-2 አሰላለፍ እየተጫወቱ ይገኛሉ።

20′ መከላከያ ቡናን ከረታው ስብስብ ምንም ለውጥ ሳያደርግ ወደ ሜዳ ሲገባ በቅዱስ ጊዮርጊስ ታደለ መንገሻ ወደ ተጠባባቂ ወርዶ በአቡበከር ተተክቷል።

16′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከመከላከያ የተከላካይ ጀርባ ኳስ በተደጋጋሚ በመጣል የግብ እድል ለመፍጠር እየሞከሩ ነው። አቤል ያለው በዚህ ሂደት የተገኘውን ኳስ ከሳጥኑ ጠርዝ መትቶ ለጥቂት በግቡ አናት ወደላይ ወጥቶበታል። 

15′ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በተለምዶ ግራ ጥላፎቅ እና ካታንጋ አካባቢ በመሰባሰብ እየደገፉ ይገኛሉ። ሆኖም አመዛኙ የስታድየሙ ክፍል ተመልካች አልባ ነው። 

14′ ናትናኤል ከግማሽ ጨረቃ ላይ የመታው ኳስ በተከላካዮች ሲደረብበት በድጋሚ መትቶ በግቡ የቀኝ ቋሚ በኩል ወደ ውጪ ወጥቷል።

12′ ጌታነህ ያሳለፈለትን ኳስ ነፃ አቋቋም ላይ የነበረው አቤል ወደ ግብ ሳይሞክረው አበበ አስጥሎታል።

10′ ጨዋታው እስካሁን በሁለቱም በኩል ወጥ እንቅስቃሴ እየታየበት አይገኝም። 


09:14 – ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀመረ።


09:10 – ቡድኖቹ ሜዳ ገብተው ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ።


09:00 የዋልያዎቹ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በስታድየሙ ተገኝተዋል።


08:55 ቡድኖቹ እና ዳኞች ማማሟቂያቂያቸውን አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል።


08:40 – ሁለቱም ቡድኖች እንዲሁም የጨዋታው ዳኞች ሜዳ ገብተው በማሟሟቅ ላይ ይገኛሉ።


አሰላለፍ

ቅዱስ ጊዮርጊስ


1 ለዓለም ብርሃኑ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
15 አስቻለው ታመነ
23 ምንተስኖት አዳነ
3 መሀሪ መና
26 ናትናኤል ዘለቀ
20 ሙሉዓለም መስፍን
18 አቡበከር ሳኒ
16 በኃይሉ አሰፋ
29 ጌታነህ ከበደ
10 አቤል ያለው


ተጠባባቂዎች


22 ባህሩ ነጋሽ
5 ዮሀንስ ዘገየ
21 ፍሬዘር ካሳ
14 ኄኖክ አዱኛ
11 ጋዲሳ መብራቴ
17 አሜ መሐመድ
27 ታደለ መንገሻ

መከላከያ


22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
2 ሽመልስ ተገኝ
16 አዲሱ ተስፋዬ
4 አበበ ጥላሁን
3 ዓለምነህ ግርማ
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
7 ፍሬው ሰለሞን
19 ሳሙኤል ታዬ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
9 ተመስገን ገብረኪዳን
14 ምንይሉ ወንድሙ


ተጠባባቂዎች


1 አቤል ማሞ
12 ምንተስኖት ከበደ
5 ታፈሰ ሰርካ
21 በኃይሉ ግርማ
8 አማኑኤል ተሾመ
11 ዳዊት ማሞ
24 አቅሌሲያስ ግርማ


ዳኞች


ዋና ዳኛ | በላይ ታደሰ
1ኛ ረዳት | ክንፈ ይልማ
2ኛ ረዳት | አበራ አብርደው


ተጨማሪ መረጃዎች


ውድድር | የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ
ቦታ | ሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም (ሀዋሳ)
ሰዓት | 09:00


ጤና ይስጥልን!

የ2010 የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ መካከል ይከናወናል። ጨዋታውን በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት እንድትከታተሉም እንጋብዛለን።

መልካም ቀን!