ዲዲዬ ጎሜስ በኢትዮጵያ ቡና ውላቸውን አራዘሙ

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የኢትዮጵያ ቡናን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ ዲዲዬ ዳሮሳ ጎሜስ በክለባቸው ኢትዮጵያ ቡና ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ዛሬ ተፈራርመዋል።

አሰልጣኙ አንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት ቢኖራቸውም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታትን በክለቡ ለመቆየት ተስማምተዋል። በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እስከ ሐምሌ 2013 (ጁላይ 2021) ድረስ ይቆያሉ ማለት ነው።

አሰልጣኝ ዲዲዬ አዲሱን ኮንትራታቸውን በሚመለከት ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለጹት “ክለቡ እምነቱን ላሳደረብኝ እጅግ በጣም ተደስቻለው ያለኝንም ሁሉ ለክለቡ ሳልሰስት ለመስጠት ተዘጋጅቻለው።” ብለዋል። አያይዘውም ” በክለቡም በሃገሪቱም በጣም ደስተኛ ስለሆንኩ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቻለው” ብለዋል።