የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር በክረምቱ የለቀቁበትን በርካታ ተጫዋቾች ለመተካት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ቀጥሎ ተስፋዬ መላኩን አስፈርሟል።
ተሰፋዬ በ2007 ክረምት ወላይታ ድቻን ለቆ ወደ ኤሌክትሪክ ካመራ በኋላ ያለፉትን ሦስት የውድድር ዘመናት ያሳለፈ ሲሆን ከሊጉ የወረደውን ክለብ ለቆ ወደ ቻምፒዮኖቹ አምርቷል። በግራ ተከላካይ እና የመሐል ተከላካየ ስፍራ መጫወት የሚችለው ተስፋዬ የጅማ የተከላካይ መስመር አማራጭን ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ተስፋዬ መላኩ በኤሌክትሪክ አብሯቸው የተጫወቱት አወት ገ/ሚካኤል እና ዲዲዬ ለብሪን በጅማ የሚያገኝ ይሆናል።