መከላከያ እና ሀዋሳ ከነማ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ አለፉ

ዛሬ በተደረጉት ሁለት የ2007 የኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች መከላከያ እና ሀዋሳ ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ለፍፃሜ በቅተዋል፡፡ በ9፡00 የተገናኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ነበሩ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ጨዋታው በተጀመረ በ4ኛው ደቂቃ በአዳነ ግርማ አማካኝነት ግብ በማስቆጠር 1-0 መምራት ሲችሉ በመጀመርያዎቹ 15 ደቂቃዎችም ተደጋጋሚ የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል፡፡ በተለይም ብሪያን ኡሞኒ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ መትቶ አግዳሚ የመለሰበትና ከጥቂት ደቂዎች በኋላ ከተመሳሳይ ቦታ መትቶ ወደ ውጭ የወጣበት ኳስ ይጠቀሳሉ፡፡

ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው ሪትም መግባት የቻሉት መከላከያዎች በ38ኛው ደቂቃ በተከላካዩ አዲሱ ተስፋዬ አማካኝነት አቻ መሆን ችለዋል፡፡ ከድቻ ከተዛወረ በኋላ ለመከላከያ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደረገው አዲሱ በመጀመርያ ጨዋታው ግብ ማስቆጠርም ችሏል፡፡ ከእረፍት መልስ ጨዋታው ኃይል የተቀላቀለበት ሲሆን መከላከያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ብልጫን መቀውሰድ ችሏል፡፡ በ60ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የተሸገረውን ኳስ በኃይሉ በግንባሩ በመግጨት ወደ ግብ ቀይሮ መከላከያን ለአሸንፊነት አብቅቷል፡፡

በጨዋታው የመከላከያው ቴዎድሮስ በቀለ በእጁ ላይ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል፡፡ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የተወሰኑ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ከተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ጋር መጠነኛ ግጭት ውስጥ ሲገቡ ታይተዋል፡፡

11፡25 የተጀመረው የሀዋሳ ከነማ እና ወላይታ ድቻ ከተጠበቀው በታች በሆነ ሁኔታ ቀዝቃዛ ጨዋታ ተስተናግዶበታል፡፡ በተለይም በመጀመርያው አጋማሽ ጨዋታው ፉክክር አልባ እና በርካታ የግብ ሙከራዎች አልታዩም ነበር፡፡ ወላይታ ድቻዎች በተለይም በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ወደ ግብ በመድረስ በኩል የተሸሉ የነበሩ ሲሆን ሀዋሳ ከነማዎች ጨዋታውን በመቆጣጠር ረገድ የተሸሉ ነበሩ፡፡

የሁለተኛው አጋማሽ በግብ ሙከራዎችም ሆነ በፉክክር ከመጀመርያው አጋማሽ የተሻለ ነበር፡፡ ሀዋሳ በጋዲሴ መብራቴ እና አመለ ሚልኪያስ ድቻ ደግሞ በአላዛር አማካኝነት የግብ ሙከራዎች ማድረግ ቢችሉም በጨዋታው ልዩነት የፈጠረችው ግብ የተገኘችው በ79ኛው ደቂቃ ነው፡፡ በክረምቱ ወደ ሀዋሳ ከነማ የተመለሰው በረከት ይስሃቅ ከጋዲሴ መብራቴ የተሸገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ሀዋሳን ወደ ፍፃሜው መርቶታል፡፡ ሀዋሳ ከነማ ከ2000 ዓ.ም በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ለመካፈል በቅቷል፡፡ መከላከያ ይህንን ጨዋታ ጨዋታው ጥሩ ነው እንደተለማመድነው ሁለተታችንም ጋርለማሸነፍ የነበረው ጥረት ከፍተኛ ነበር፤፤ ከተሸነፍክ መውደቅህ ስለማይቀር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋ እንደመሆኑ ከባድ ጉልበት የሚፈልግ ነው፡፡ ሜዳውም ምቹ አልነበረም፡፡

ያጋሩ