የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ – ቀጥታ ስርጭት

ማክሰኞ ጥቅምት 13 ቀን 2011


FT ጅማ አባጅፋር 1-1 መከላከያ

⚽️23′ ኤልያስ ማሞ ⚽️59′ ሳሙኤል ታዬ

🏆 መከላከያ በመለያ ምቶች 4-2 አሸንፎ የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡

መከላከያ – ምንይሉ ወንድሙ  አስቆጠረ፡፡ 2-4


ጅማ አባ ጅፋር – ዲዲዬ ለብሪ አስቆጠረ 2-3

መከላከያ – ተመስገን ገብረኪዳን አስቆጠረ 1-3


ጅማ አባ ጅፋር – ንጋቱ ገብረስላሴ ሳተ 1-2

መከላከያ – አዲሱ ተስፋዬ አስቆጠረ 1-2


ጅማ አባ ጅፋር – ከድር ኄረዲን ሳተ 1-1

መከላከያ – ሽመልስ ተገኝ ሳተ – 1-1


ጅማ አባጅፋር – ኤርሚያስ ኃይሉ አስቆጠረ 1-1

መከላከያ – አበበ ጥላሁን አስቆጠረ 0-1


⏰ ተጠናቀቀ!
አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት አምርቷል፡፡


90+3 ጅማዎች የጨዋታው የመጨረሻ ዕድል የሚመስል ቅጣት ምት ከግራው የሳጥን ጠርዝ ትንሽ ፈቀቅ ብሎ አግኝተዋል። ይሁን ቅጣት ምቱን አሻማ … መከላከያዎች በግንባር አወጡት።

90+1 ዳዊት እስጢፋኖስ ከመሀል ሜዳ ባሻገረው ቅጣት ምት በሀይሉ ከሳጥን ውጥ በግንባሩ ሞክሮ ኤጄዬ አስኖበታል።

ጭማሪ ደቂቃ – 3

86′ ሲሴኮ በሰራው ጥፋት በግምት ከ20 ሜትር ርቀት የተሰጠውን ቅጣት ምት ምንይሉ ቢመታም ኳስ በቀጥታ ወደ አጄይ እጆች አምርታለች።

85′ ቢጫ ካርድ – አዳማ ሲሴኮ

80′ ተመስገን ከሳጥኑ የቀኝ ጠርዝ ላይ የሞከረው ኳስ በተመሳሳይ መልኩ በላይ በኩል ወጥቷል።

77′ ይሁን ከሳጥን ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ ከግቡ አግዳሚ በላይ ወጥቷል።

76′ የተጫዋች ቅያሪ – ጅማ አባ ጅፋር
« ኤልያስ ማሞ – ወጣ
» ንጋቱ ገብረስላሴ – ገባ


75′ የተጫዋች ቅያሪ – መከላከያ
« ዓለምነህ ግርማ – ወጣ
» ተመስገን ገብረኪዳን – ገባ


73′ ብሩክ እና ኤርሚያስ ከመሀል ሜዳ በከፈቱት መልሶ ማጥቃት በግራ መስመር ከኤርሚያስ ኳስ የደረሰው ዲዲዬ ለብሪ የሞከረው ኳስ ለጥቂት በጎን ወጥቷል።


71′ የተጫዋች ቅያሪ – ጅማ አባ ጅፋር
« አስቻለው ግርማ – ወጣ
» ብሩክ ገበረዓብ – ገባ

68′ ጅማዎች ኳስ ይዘው ተጭነው በጦሩ ሜዳ ላይ ለመጫወት እየሞከሩ ነው ፤ መከላከያዎች ለብቸኛው አጥቂ ምንይሉ ኳሶችን ማሻገር ምርጫቸው ያደረጉ ይመስላል።


61′ የተጫዋች ቅያሪ – መከላከያ
« ፍሬው ሰለሞን – ወጣ
» ዳዊት ማሞ – ገባ


⚽️ 59′ ጎል ! ሳሙኤል ታዬ
ከሳጥን ውጪ የተላከው እና ተጨርፎ በጅማ ሳጥን ውስጥ የደረሰውን ኳስ ሳሙኤል ታዬ አስቆጥሮ መከላከያን አቻ አድርጓል።


55′ ፍሬው ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ አክርሮ ለመምታት ጥሩ የሚባል አጋጣሚ ቢያገኝም ሙከራው የተጠበቀውን ያህል ኃይል ሳይኖረው በአጄዬ ተይዟል።

54′ ኤልያስ ከሳጥን ውጪ የመታት ኳስ አዲሱን ጨርፋ አቤልን በማለፍ ግብ ለመሆን ብትቃረብም የግቡ አግዳሚ መልሷታል።

50′ ሁለቱም ቡድኖች ከመጀመሪያው አጋማሽ ሲነፃፀር ቀጥተኛ በሆኑ ኳሶች አጥቂዎቻቸውን ለማግኘት እየሞከሩ ነው።

12:22 ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ


⏰ እረፍት!

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

40′ ምንይሉ በግራ መስመር ከዳንኤል አጄዬ ጋር ተገናኝቶ ቺፕ ለማድረግ የሞከረው ኳስ ወደ ላይ ተነስቶበታል።


37′ የተጫዋች ቅያሪ – ጅማ አባ ጅፋር
« አክሊሉ ዋለልኝ – ወጣ
» ዲዲዬ ለብሪ – ገባ


32′ የተጫዋች ቅያሪ – መከላከያ
« ፍፁም ገብረማርያም – ወጣ
» በሀይሉ ግርማ – ገባ


26′ ቀይ ካርድ – ቴዎድሮስ ታፈሰ
መሀል ሜዳ ላይ ቴዎድሮስ አስቻለውን በክርኑ በመማታቱ ቀጥታ ቀይ ካርድ ተመልክቷል። ተጫዋቹ በእንባ ታጅቦ ከሜዳ ወጥቷል።


25′ ምንይሉ ከግራ መስመር ያሻገረውን ኳስ ሳሙኤል ከቅርብ ርቀት በተመቻቸ አቋቋም ላይ ሆኖ በግንባሩ ቢሞክርም ዳንኤል አጄዬ ይዞበታል::


23′ ⚽️ ጎል! ኤልያስ ማሞ
ጅማዎች በቀኝ መስመር ከከፈቱት ጥቃት ኤርሚያስ ከዐወት የተቀበለውን ኳስ ወደ ሳጥን ውስጥ መሬት ለመሬት ልኮለት ኤልያስ ማሞ በድንቅ አጨራረስ የመጀመሪያ ግብ አስቆጥሯል።


20′ በሳሙኤል ታዬ የቀኝ መስመር ጥቃት መነሻነት ምንይሉ ከዳዊት የተቀበለውን ኳስ ከሳጥኑ መግቢያ ላይ ሞክሮ በግቡ አናት ወጥቶበታል።

15′ ጅማ አባ ጅፋሮች በተሻለ የኳስ ቁጥጥር ድርሻ በመከላከያ ሜዳ ላይ ይታያሉ። ሆኖም እስካጉን ጨዋታው አስደንጋጭ ሙከራ አላስተናገደም።

7′ አባ ጅፋር በኤርሚያስ እንዲሁም መከላከያ በፍፁም አማካይነት ወደ ግብ ከደረሱባቸው አጋጣሚዎች ውጪ ጨዋታው በመሀል ሜዳ እንቅስቃሴ ላይ ያመዘነ ነው።

11:24 ዋንጫው ተጠግኖ ወደ ቦታው ላይ ተቀምጧል፡፡


11:19 ተጅመረ


11፡ 13 የዕለቱ የክብር እንግዶች ተጫዋቾችን በመተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።

11:10 ዋንጫው በንፋስ ምክንያት ወድቆ የመሸረፍ አደጋ ደርሶበታል፡፡


አሰላለፍ

ጅማ አባ ጅፋር


29 ዳንኤል አጄይ
27 ዐወት ገብረሚካኤል
15 አዳማ ሲሶኮ
4 ከደር ኸይረዲን
14 ኤልያስ አታሮ
19 አክሊሉ ዋለልኝ
26 ኄኖክ ገምቴሳ
6 ይሁን እንዳሻው
10 ኤልያስ ማሞ
9 ኤርሚያስ ኃይሉ
17 አስቻለው ግርማ


ተጠባባቂዎች


30 ዘሪሁን ታደለ
13 ተስፋዬ መላኩ
15 ያሬድ ዘውድነህ
21 ንጋቱ ገ/ስላሴ
3 መስዑድ መሀመድ
11 ብሩክ ገብረዓብ
31 ዲዲዬ ለብሪ

መከላከያ


1 አቤል ማሞ
2 ሽመልስ ተገኝ
4 አበበ ጥላሁን
26 አዲሱ ተስፋዬ
3 ዓለምነህ ግርማ
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
7 ፍሬው ሰለሞን
19 ሳሙኤል ታዬ
14 ምንይሉ ወንድሙ
27 ፍፁም ገብረማርያም


ተጠባባቂዎች


22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
5 ታፈሰ ሰረካ
12 ምንተስኖት ከበደ
21 በኃይሉ ግርማ
8 አማኑኤል ተሾመ
11 ዳዊት ማሞ
9 ተመስገን ገብረኪዳን


ዳኞች


ዋና ዳኛ | ቴዎድሮስ ምትኩ
1ኛ ረዳት | ትግል ግዛው
2ኛ ረዳት | ተመስገን ሳሙኤል


ውድድር | የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ
ቦታ | አዲስ አበባ ስታድየም
ሰዓት | 11:00