በ2009 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የነበረውና በ2010 የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ተፎካካሪ ክለብ የነበረው ጅማ አባ ቡና ደቡብ ፖሊስን ተከትሎ ምድቡን በሁለተኛነት በማጠናቀቅ በመለያ ጨዋታው በሽረ እንዳሥላሴ ተሸንፎ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሳያድግ መቅረቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
ክለቡ በ2010 የውድድር ዘመን በፋይናንስ ቀውስና በቡድኑ ውስጥ ባሉ አስተዳደራዊ ክፍተቶች ምክንያቶች እየተንገታገተ የውድድር ዘመኑን ሲያጠናቅቅ ዘንድሮም የክለቡ ህልውና አጠያያቂ ደረጃ መድረሱና እጣፈንታ ምን ይሆን የሚለው የክለቡን ደጋፊዎች ያሳሰበ፤ በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ደግሞ የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ እንደነበረው ንግድ ባንክ የመፍረስ አደጋ ይደርስበታል ተብሎ የተፈራ ቢሆንም ጅማ አባ ቡና በ2011 የውድድር ዘመን በመካከለኛና ደቡብ ምዕራብ ምድብ እንደሚሳተፍ ተረጋግጧል፡፡
ክለቡንም በቀጣይ አንድ ዓመት በአሰልጣኝነት እንዲመሩ መኮንን በቀለን ሾሟል። አሰልጣኝ መኮንን ከዚህ ቀደም በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ፊንጫ ስኳር፣ ሻሸመኔ ከተማ እና ቡራዩ ከተማ የሰሩ ሲሆን ቡራዩን ከለቀቁ በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት ያለ ስራ አሳልፈው ቆይተዋል።
አሰልጣኝ መኮንን በቀለ በቀጣይ ቡድኑን የማዋቀርና ጅማ አባቡናን ለፕሪምየር ሊግ ተሳተፊ የማድረግ ሀላፊነት የተጣለባቸው እንደመሆኑ በክረምቱ ቡድኑን በለቁት በርካታ ወሳኝ ተጫዋቾች ምትክ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እንደሚቀላቅሉ ይጠበቃል፡፡
በተያያዘ ዜና ክለቡ የአሰልጣኝ መክንን ረዳት ሆነው እንዲሰሩ ለማ ተሾመን መቅጠሩ ታውቋል።
ማስታወቂያ |
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ |