ካሜሩን ለምታስተናግደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረጉ የማጣርያ ጨዋታዎች በኅዳር ወር ሲቀጥሉ ኢትዮጵያ በ4ኛ የምድብ ጨዋታዋ ኅዳር 9 ጋናን በአዲስ አበባ ስታድየም ታስተናግዳለች፡፡
ዋሊያዎቹ ለጨዋታው የሚረዳቸውን ዝግጅት ከማክሰኞ ጥቅምት 27 ጀምሮ ሲያከናውኑ ለዚህም 23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከኬንያ በተከታታይ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ የቡድኑ አካል ያልነበሩ በርካታ ተጫዋቾች የተመረጡ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡናው ዳንኤል ደምሴ ለመጀመርያ ጊዜ ጥሪ ደርሶታል። በቀጣይ በውጪ ሀገራት የሚጫወቱት ተጫዋቾች የጨዋታው ዕለት ሲቃረብ ቡድኑን ይቀላቀላሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
ግብ ጠባቂዎች (2)፡ አቤል ማሞ (መከላከያ)፣ ሳምሶን አሰፋ (ድሬዳዋ ከተማ)
ተከላካዮች (8)፡ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አብዱልከሪም መሐመድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አበበ ጥላሁን (መከላከያ)፣ ደስታ ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ አንተነህ ተስፋዬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከነማ)፣ ተመስገን ካስትሮ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)
አማካዮች (4)፡ ሙሉዓለም መስፍን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ከነዓን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)፣ ዳንኤል ደምሴ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሳምሶን ጥላሁን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሽመልስ በቀለ (ፔትሮጄት/ግብፅ)፣ ጋቶች ፓኖም (ኤል ጎውና/ግብፅ)፣ ቢኒያም በላይ (ስከንደርቡ/አልባንያ)
አጥቂዎች (5)፡ ምንይሉ ወንድሙ (መከላከያ)፣ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ጌታነህ ከበደ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል (መቐለ 70 እንደርታ)፣ ዑመድ ኡኩሪ (ስሞሀ/ግብፅ)