የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን በ2017 ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት አህጉራዊ የክለብ ውድድሮች በአንድ የካላንደር ዓመት (ጃንዋሪ-ዲሴምበር) መካሄዳቸው ቀርቶ ከኦገስት-ሜይ በሚደረግ የውድድር አካሄድ መቀየሩ ይታወሳል፡፡ ዘንድሮ (2018) ለመጨረሻ ጊዜ በቀድሞው ፎርማት ተካሂዶም በትላንትናው ዕለት በኤስፔራንስ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
አዲሱ የካላንደር ፎርማት ከቀጣዩ የውድድር ዘመን (2019/20) ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ዘንድሮ ግን ከሁለት ሳምንት በኋላ ተጀምሮ ሜይ ወር ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ካለፉት ውድድሮች በተለየም ዘንድሮ ጨዋታዎች በተቀራራቢ የጊዜ ልዩነቶች ይካሄዳሉ፡፡
ካፍ ባሳለፍነው ሳምንት የቅድመ ማጣርያ እና የመጀመርያ ዙር ድልድል አውጥቶ የነበረ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ይፋዊ በሆነ መንገድ በድረ-ገጹ ላይ ያስታወቀው በትላንትናው ዕለት ነበር፡፡ በድልድሉ መሰረት የኢትዮጵያው ቻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር ከጅቡቲው ቴሌኮም ጋር በቅድመ ማጣርያው ይጫወታል፡፡ የመጀመርያው ጨዋታ ጅቡቲ ላይ ሲከናወን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡ አባ ጅፋር ይህንን ጨዋታ በድል ከተወጣ በመጀመርያው ዙር የ2018 የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚው አል-አህሊን የሚገጥም ይሆናል፡፡
ሙሉ ድልድሉ ይህን ይመስላል፡-
ቅድመ ማጣርያ ዙር ቅድሚያ የተጻፉት ክለቦች የመጀመርያውን ጨዋታ በሜዳቸው ያደርጋሉ |
||
ዲያራፍ |
1 | |
ኤኤስ ሳውራ |
2 | |
ኢቲሀድ ታንገር |
3 | |
ለሜ. ንጎዚ |
4 | |
ቦቦ ዲዮላሶ |
5 | |
ሶኒዴፕ |
6 | |
ኦ. ፓያሬትስ |
7 | |
ቮልካን ክለብ |
8 | |
ኖውህዲቦ |
9 | |
ሌኦኔስ ቪ. |
10 | |
ጎር ማሒያ |
11 | |
ዴሎም |
12 | |
ዩዲ ሶንጎ |
13 | |
ሲምባ |
14 | |
ጅቡቲ ቴሌኮም |
15 | |
ኮንስታንቲን |
16 | |
ኤል ሜሪክ |
17 | |
ስታደ ሴ.አፍረካኔ |
18 | |
አሴክ ሚሞሳ |
19 | |
ታውንሺፕ ሮለርስ |
20 | |
ኤፒአር |
21 | |
አል ሒላል |
22 | |
አል ናስር |
23 | |
ሆሮያ |
24 | |
ፕ. ዲ. አጉስቶ |
25 | |
ሲናፕስ |
26 | |
የመጀመርያ ዙር ቅድሚያ የተጻፉት ክለቦች የመጀመርያውን ጨዋታ በሜዳቸው ያደርጋሉ |
||
ዋይዳድ ካሳ. | 27 | ጨዋታ 1 አሸናፊ |
ጨዋታ 2 አሸናፊ | 28 | ጨዋታ 3 አሸናፊ |
ጨዋታ 4 አሸናፊ | 29 | ጨዋታ 5 አሸናፊ |
ቲፒ ማዜምቤ |
30 | ጨዋታ 6 አሸናፊ |
ጨዋታ 7 አሸናፊ | 31 | ጨዋታ 8 አሸናፊ |
ጨዋታ 9 አሸናፊ | 32 | ጨዋታ 10 አሸናፊ |
ጨዋታ 11 አሸናፊ | 33 | ጨዋታ 12 አሸናፊ |
ጨዋታ 13 አሸናፊ | 34 | ጨዋታ 14 አሸናፊ |
አል አህሊ |
35 | ጨዋታ 15 አሸናፊ |
ጨዋታ 16 አሸናፊ | 36 | ጨዋታ 17 አሸናፊ |
ጨዋታ 18 አሸናፊ | 37 | ጨዋታ 19 አሸናፊ |
ኤስ ቪታ |
38 | ጨዋታ 20 አሸናፊ |
ጨዋታ 21 አሸናፊ | 39 | ጨዋታ 22 አሸናፊ |
ጨዋታ 23 አሸናፊ | 40 | ጨዋታ 24 አሸናፊ |
ጨዋታ 25 አሸናፊ | 41 | ጨዋታ 26 አሸናፊ |