ኢትዮጵያ ከ ሶማሊያ – ቀጥታ ስርጭት

ረቡዕ ኅዳር 5 ቀን 2011
FT ኢትዮጵያ🇪🇹 4-0 🇸🇴ሶማሊያ
28′ ከዓን ማርክነህ
39′ እስራኤል እሸቱ
66′ አማኑኤል ገብረሚካኤል
70′ አቡበከር ሳኒ



ተፈፀመ

90+1 አቤል እንዳለ ከአማኑኤል ግልፅ የግብ ማግባት አጋጣሚ ቢፈጠርለትም ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

84′ የተጨዋች ለውጥ – ሶማሊያ
አንዋር ሻኩንዳ (ወጣ)
ኢስማኤል አብዲ (ገባ)

ጭማሪ ደቂቃ – 4

84′ የተጨዋች ለውጥ – ሶማሊያ
ኑኔ አህመድ (ወጣ)
መሀድ ሙሀመድ (ገባ)

81′ የተጨዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
እስራኤል እሸቱ (ወጣ)
አቤል እንዳለ (ገባ)

75′ አቡበከር ሳኒ – ቀይ
አቡበከር ሳኒ መሀመድ ዓሊ በረጅሙ የተሻማን ኳስ በግንባሩ ለመግጨት በሞከረበት አጋጣሚ በእግሩ አደገኛ ጥፋት በመስራቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

ጎል!!! አቡበከር ሳኒ
70′ ከቴዎድሮስ ታፈሰ የተነሳውን ኳስ ከነዓን ወደ ሳጥን ይዞ ገብቶ ያቀበለውን አቡበከር ወደ ግብነት ቀይሮታል።

68′ ፈርሀን አህመድ (ቢጫ)

68′ የተጨዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
ዳዊት ማሞ (ወጣ)
አቡበከር ሳኒ (ገባ)

ጎል!!!አማኑኤል ገብረሚካኤል (ፍ.ቅ.ም)
66′ አብዱዌሊ መሀመድ በአማኑኤል ላይ የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ራሱ አማኑኤል አስቆጥሯል።

62′ ኢሴ ኢብራሂም (ቢጫ)

59′  የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
ሀብታሙ (ወጣ)
አማኑኤል (ገባ)

58′ አቶሽ ከርቀት አክሮ በመምታት ያደረገውን አደገኛ ሙከራ ተክለማሪያም አውጥቶበታል።

54′  የተጫዋች ለውጥ – ሶማሊያ

ፋይሰል ሀሺ (ወጣ)

ፈርሀን አህመድ (ገባ)

52′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከመጀመሪያውም በተሻለ ሁኔታ በተጋጣሚው ሜዳ ላይ በመቆየት ጫና ፈጥሮ እየተጫወተ ይገኛል።

49′ ሀሺ ከርቀት የመታውን ኳስ ተክለማሪያም ሳይቸገር ይዞበታል።

11:06 ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ


እረፍት

ጭማሪ ደቂቃ – 2

ጎል!!!!!እስራኤል እሸቱ
39′ ቴዎድሮስ ታፈሰ በተከላካዮች መሀከል ያሳለፈለትን ኳስ በመጠቀም እስራኤል ሁለተኛ ግብ አስቆጥሯል።

34′ የጨዋታው ፍጥነት ቀነስ ብሎ የቀጠለ ሲሆን ሱማሊያዎች በቀኝ መስመር ተሰላፊው ሀሺ አማካይነት የመልሶ ማጥቃት ዕድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ኢትዮጵያዊያኑ ኳስ መስርተው በመግባት በሁለቱ ኮሪደሮች በኩል ለማጥቃት እየሞከሩ ይገኛሉ።

ጎል!!!!!! ከነዓን ማርክነህ
28′ በቀኝ የማዕዘን መምቻ በበረከት ላይ በተሰራ ጥፋት የተሰጠውን የቅጣት ምት ዳዊት ማሞ ሲያሻማ ከነዓን ከግቡ አፋፍ ላይ አስቆጥሯል።

23′ ከነዓን ማርክነህ የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

21′ ዳዊት ማሞ ከግራ የሳጥኑ ጠርዝ ላይ ከተገኘ ቅጣት ምት ያደረገውን ሙከራ ግብጠባቂው ዓሊ አድኖበታል።

18′ አጥቂዎቹ አሽቶ እና ሻኩንዳ ጥሩ የመልሶ ማጥቃት አጋጣሚ ቢያገኙም ቅብብላቸው በኢትዮጵያ ተከላካዮች ተበላሽቷል።

16′ እስራኤል ከከንዓን ኳስ ተቀብሎ በቀኝ በኩል ወደ ሳጥን ከገባ በኋላ አክርሮ የመታው ኳስ ለጥቂት በሶማሊያ ግብ የቀኝ ቋሚ በኩል ወጥቷል።

10′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከመጀመሪያው ሙከራ ባለፈ በበረከት እና ሀብታሙ አማካይነት ከርቀት ሙከራዎችን ሲያደርግ የጨዋታው እንቅስቃሴ ተመጣጣኝ የሚባል ነው።

3′ ሳሙኤል የሰጠውን ኳስ ከንዓን ወደ ሳጥን ይዞ በመግባት ሞክሮ ኳስ የግቡን አግዳሚ ታካ ወጥታለች።

10:03 ጨዋታው ተጀመረ!


09፡56 የሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ መዝሙሮች እየተዘመሩ ነው::

[AdSense-B]


አሰላለፍ
ኢትዮጵያ ሶማሊያ
1 ተክለማሪያም ሻንቆ
13 ገናናው ረጋሳ
4 ተመስገን ካስትሮ
5 ፍቃዱ ደነቀ
12 ሳሙኤል ዮሀንስ
15 ታዎድሮስ ታፈሰ
8 ከንዓን ማርክነህ
14 በረከት ደስታ
11 ዳዊት ማሞ
17 ሀብታሙ ገዣኸኝ
9 እስራኤል እሸቱ
1 ሰዒድ ዓሊ
17 አብዱዌሊ መሀመድ
3 መሀመድ ዓሊ
5 አህመድ አብዲ
4 ኢሴ ኢብራሂም (አ)
6 ሀሰን ጌይሴ
8 ኑኔ አህመድ
7 ፌይሰል ሀሰን
11 ፋይሰል ሀሺ
10 አብዲአዚዝ አቶሽ
16 አንዋር ሻኩንዳ
ተጠባባቂዎች ተጠባባቂዎች
18 ፂዮን መርዕድ
2 ፈቱዲን ጀማል
16 ሸዊት ዮሃንስ
20 የአብስራ ተስፋዬ
22 አቤል እንዳለ
7 አበበከር ሳኒ
10 አማኑኤል ገብረሚካኤል
20 አባስ ሀሺ
2 ዓሊ ሀሰን
9 ፈርሀን አህመድ
12 ቢሌ ወሂሊ
14 መሀድ ሙሀመድ
15 ዑመር በነው
18 ኢስማኤል አብዲ
ዳኞች
 ዋና – ጉዊራት ሀይተም (ቱኒዚያ)
1ኛ ረዳት – ራምዚ ኸርች (ቱኒዚያ)
2ኛ ረዳት – ኸሊል ሀሳኒ (ቱኒዚያ)
ውድድር  | የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ
ቦታ |  አዲስ አበባ ስታድየም
ሰዓት | 10:00

ጤና ይስጥልን

ወደ 2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚያልፉ ሀገራትን ለመለየት የሚደረገው የአህጉራት ከ23 ዓመት በታች ውድድር የአፍሪካ ዞን ማጣርየ በዛሬው ዕለት ሲጀመር ኢትዮጵያ በቅድመ ማጣያው የመጀመርያ ጨዋታ ሶማሊያን ታስተናግዳለች፡፡ ከ10፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታድየም የሚደረገውን ይህን ጨዋታም በቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት በሶከር ኢትዮጵያ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

መልካም ቆይታ