ሳላዲን ለምንያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ አልታወቀም

ባለፈው እሁድ በተደረገው የግብፅ ሱፐርካፕ ፍልሚያ ላይ ለአዲሱ ክለቡ አልአህሊ ለመጀመር ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተው ሳላዲን ሰኢድ በጨዋው 73ኛ ደቂቃ ባጋጠመው ጉዳት ከሜዳ ተቀይሮ ወጥቷል፡፡

ሳላዲን ከጨዋታው በኋላ በእግሩ ጡንቻዎች ላይ ምርመራ ያደረገ ሲሆን የአል-አህሊ ዶክተር ዶ/ር ኢሃብ አሊ ከምርመራው ውጤት በኋላ ለምን ያህል ጊዜ ከጨዋታ እንደሚርቅ እንደሚያስታውቁ ክለቡ በድረገፁ አስታውቋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ አምበል ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከ3 ሳምንት በኋላ ማሊን ለምትገጥምበት ጨዋታ በማርያኖ ባሬቶ ጥሪ ተደርጎለታል፡፡

ያጋሩ