የሚጠበቅብንን አድርገን አሸንፈን እንደምንመለስ ለፕሬዝዳንታችን ቃል ገብተንለታል – አሳሞአ ጂያን

በካሜሩን የ2019 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ዛሬ ኢትዮጵያ እና ጋና 10:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም ይጫወታሉ። የጋና ብሔራዊ ቡድን ከዛሬው ጨዋታ በፊት በትላንትናው እለት የመጨረሻ ልምምዱን ባደረገበት ወቅት የቡድኑ አምበል አሳሞአ ጂያን ስለ ጨዋታው አስተያየቱን ሰጥቷል። እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ስለጨዋታው

የምንጫወተው ከባለሜዳ ጋር እንደመሆኑ መጠን እኛ ላይ ጫና አለው፡፡ ቁጥሮችን በመመልከት ማንም ቢሆን ጋና እንደምታሸንፍ ሊገምት ይችል ይሆናል። ነገር ግን ውጤቱ የሚታወቀው ከ90 ደቂቃ በኋላ ነው፡፡

በኬንያ የነበረው ዝግጅት

ዝግጅት በጣም ጥሩ ነበር የሁላችንም ዓላማ ይህን ጨዋታ በድል መወጣት ነው፡፡ ሁሉም ተጫዋቾች ከአድካሚ ጉዞ ነው የመጡት ድካም አለ፤ ነገር ግን አጭርም ቢሆን በሚገባ ተዘጋጅተናል፡፡ ሁላችንም ለጨዋታው ዝግጁ ነን፤ ጉዳት የለብንም። የሚጠብቅብን ለማድረግ ነው እዚ የመጣነው፡፡

የፕሬዝዳንቱ ልምምድ ሜዳ መምጣት የሚፈጥረው ስሜት 

ሁላችንም እንደቡድን ነው የምንጫወተው የፕሬዝዳንታችን መምጣት በራስ መተማመን ይጨምራል፤ ለሱም የመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል በልምምድ ሜዳ ላይ መቶ ሲጎበኘን፤ ይሄ ለኛም ቢሆን ለነገው ጨዋታ ኃይል ይሆነናል፡፡ የምንጫወትው ከባለሜዳ ክለብ ጋር ነው ስለዚ ቀላል ነገር አይጠብቀንም፤ ሜዳ ሙሉ ደጋፊ አላቸው፡፡ ስህተት ሳንሰራ የሚጠበቅብንን አድርገን አሸንፈን እንደምንመለስ ቃል ገብተንለታል፡፡