የ2011 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከጥቅምት 25 ወዲህ በብሔራዊ ቡድን ዝግጅት እና ሌሎች ምክንያቶች ተቋርጦ ቆይቷል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በወሰነው ውሳኔ መሰረትም በዚህ ሳምንት በከፊል የሦስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲደረጉ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሙሉ ወደፊት በሚገለፅ ቀን የሚከናወኑ ይሆናል።
በሁለተኛ ሳምንት ጥቅምት 24 እና 25 ሦስት ጨዋታዎች መካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን ክለቦች ለብሔራዊ ቡድን እና ኦሊምፒክ ቡድኑ ተጫዋቾች በማስመረጣቸውና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ሊከናወኑ የነበሩት አምስት ጨዋታዎች ማለትም ድሬዳዋ ከተማ ከ ደቡብ ፖሊስ፣ ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና፣ ባህር ዳር ከተማ ከ ስሑል ሽረ፣ አዳማ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ጅማ አባ ጅፋር ከ መከላከያ ወደፊት በሚገለጹ ቀናት የሚከናወኑ ናቸው።
በሦስተኛው ሳምንት ከሚደረጉ 8 ጨዋታዎች መካከል ግማሹ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀናት ይከናከናሉ።
የሚካሄዱ ጨዋታዎች
አርብ ኅዳር 14 ቀን 2011
ሲዳማ ቡና ከ ባህር ዳር ከተማ (09:00 ሀዋሳ)
ቅዳሜ ኅዳር 15 ቀን 2011
ደቡብ ፖሊስ ከ ደደቢት (09:00 ሀዋሳ)
እሁድ ኅዳር 16 ቀን 2011
ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ (09:00 ሀዋሳ)
ስሑል ሽረ ከ አዳማ ከተማ (09:00 ሽረ)
ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፉ ጨዋታዎች
ኢትዮጵያ ቡና ከ ወልዋሎ ዓ/ዩ
መቐለ 70 እንደርታ ከ ፋሲል ከነማ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባ ጅፋር
መከላከያ ከ ድሬዳዋ ከተማ