የመስከረም 19 ምሽት ዜናዎች

ብሄራዊ ቡድናችን አሸንፏል

ለቦትስዋና 49ኛ የነፃነት በአል አከባበር ከቦትስዋና እግርኳስ ማህበር የቀረበለትን ግብዣ ተቀብሎ ወደ ስፍራው ያመራው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ 11፡00 ላይ ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው ጨዋታ 3-2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ኢትዮጵያ በጨዋታው 2-0 እና 3-1 የመምራት እድል ያገኘች ስትሆን ዳዊት ፍቃዱ ሁለት ግቦችን እንዲሁም ስዩም ተስፋዬ አንዷን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ለቦትስዋና ሁለቱንም ግብ ዮኤል ሞጎሮሲ አስቆጥሯል፡፡

 

ናትናኤል እና ሳላዲን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን ውል አራዘሙ

ለሙከራ ወደ ፖርቱጋል አቅንተው የነበሩት ሳላዲን በርጊቾ እና ናትናኤል ዘለቀ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን ውል አራዝመዋል፡፡ ሁለቱ ተጫዋቾች የፖርቱጋል የሙከራ ጊዜያቸው ካልተሳካ የጊዮርጊስ ኮንትራታቸውን እንደሚያድሱ ቃል በገቡት መሰረት ውላቸውን በ2 አመት አድሰዋል፡፡

አሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማን ናትናኤል ዘለቀን የቡድናቸው ዋነኛ ተጫዋች የማድረግ ፍላጎት እዳላቸው መናገራቸው የሚታስ ነው፡፡

 

የከፍተኛ ሊግ ክለቦች አሰልጣኞች ለውጥ አያደረጉ ነው

የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የአሰልጣኝ ሹም ሽር እያደረጉ ነው፡፡ አሰልጣኝ ታደሰ ከአዲስ አበባ ከነማ ጋር የተለያየ ሲሆን ጳውሎስ ጌታቸውን ያሰናበተው ሱሉልታ ከነማን በድጋሚ ተረክቧል፡፡

ደቡብ ፖሊስ ክፍሌ ቦልተናን አሰናብቶ የቀድሞ የኦሜድላ ከከብ ተስፋዬ ፈጠነን አሰልጣኝ አድርጎ ሲሾም ተሰናባቹ ክፍሌ ቦልተና አሰልጣኝ ፋንታዬን ያሰናበተው ጅማ ከነማን ተረክቧል፡፡

ናሽናል ሴሜንት አዲስ አሰልጣኝ ከቀጠሩ ክለቦች አንዱ ነው፡፡ በስምኦን አባይ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሲመራ የነበረው ናሽናል ሴሜንት የቀድሞው የሀረር ቢራ ድንቅ አማካይ ተስፋዬ ተካ ‹‹ ዶቃ ››ን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል፡፡

የኢትዮጵያ ውሃ ስራ በበኩሉ አሰልጣኝ ከማል አህመድን አሰናብቶ የወራቤ ከነማ ምክትል አሰልጣኝ ነበረው ያሬድን ተክቷል፡፡

ያጋሩ