በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል የነበራቸው የወልዋሎ ተጫዋቾች አታክልቲ ፀጋዬ፣ ወግደረስ ታዬ እና መኩሪያ ደሱ ከክለቡ ጋር ኮንትራት እያላቸው አሰናብቷቸዋል በሚል ከዚህ ቀደም በዲሲፕሊን ኮሚቴ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርግ በፌዴሬሽኑ ውሳኔ ተላልፎበታል።
ተጫዋቾቹ በክረምቱ ክለቡ ቀሪ የአንድ ዓመት የውል ኮንትራት ቢኖራቸውም ከክለቡ ጋር እንደማይቀጥሉ በተሰጣቸው ደብዳቤ ክለቡን እንዲለቁ ቢወስንም ዘንድሮ የሚያጫውት ውል ያላቸው ሶስቱ ተጫዋቾች ለፌድሬሽኑ ቅሬታቸውን በማሰማታቸው ፌድሬሽኑ ተጫዋቾቹ ጥያቄያቸው ተገቢ ነው በማለት የወልዋሎን ውሳኔ በመሻር ወደ ስራቸው እንዲመለሱ እና ያልተከፈለ ደሞዛቸው በ10 ቀናት ውስጥ እንዲከፈል ማሳሰቡ የሚታወስ ነው። ሆኖም ክለቡ ውሳኔውን ተግባራዊ ባለማድረጉ ምክንያት የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተግባራዊ እስኪያደርግ ድረስ ማንኛውንም አገልግሎት ከፌዴሬሽኑ እንደማያገኝ በተከታዩ ደብዳቤ ገልጿል፡፡
ተዛማጅ ጽሁፍ ፡ወልዋሎ በሦስት ተጫዋቾቹ ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ የዲሲፕሊን ኪሚቴ ውድቅ አደረገው